Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም ለአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ተሳታፊዎች የተለያዩ አገልግሎቶችን በውጭ ሀገራት ገንዘብ እያቀረበ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ እየተሳተፉ ለሚገኙ እንግዶች የተለያዩ አገልግሎቶችን በዶላር፣ በዩሮና ድርሀም እያቀረበ እንደሚገኝ አስታወቀ።
ኢትዮ ቴሌኮም በ40ኛዉ የአፍሪካ ሕብረት ስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤትና በ35ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ባረፉባቸው ሆቴሎች፣ በቦሌ አለም አቀፍ አየር መንገድና በአፍሪካ ሕብረት ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን እየሰጠ እንደሚገኝ የድርጅቱ በኤምባሲና በአለም አቀፍ ተቋማት የፕሪሚየር ደምበኞች አገልግሎት ማናጀር አሚና ነጋሽ ገልጸዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በሕብረቱ ጉባኤ ለመሳተፍ ለመጡ እንግዶች በቀጥታ አገልግሎት የሚሰጡ ጥቅሎችና ሲም ካርዶችን አዘጋጅቷል ብለዋል።
እነዚህ አገልግሎቶች የአለም አቀፍና የሀገር ውስጥ ጥሪ፣ ኢንተርኔትና አጭር የጽሑፍ መልዕክትን ያካተቱ ናቸው ያሉት ሃላፊዋ÷ አገልግሎቶቹ ለሕብረቱ ተሳታፊዎች በዶላር በዩሮና ድርሀም የቀረቡ ናቸው ሲሉ አስታውቀዋል።
የሞባይል ሽያጭና የይሙሉ ካርድ አገልግሎትም እየተሰጠ እንደሚገኝ አንስተው÷ አገልግሎቱን ኢትዮጵያውያን የጉባኤው ተሳታፊዎች ጭምር በመግዛት እየተጠቀሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
አገልግሎቱ ጉባኤው ከተጠናቀቀ በኋላ በኢትዮጵያ ለተወሰነ ጊዜ ለሚቆዩ እንግዶች እንደሚያገለግልም ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮ ቴሌኮም በጉባኤው የኢንተርኔትና አጠቃላይ የኮሙኒኬሽን አገልግሎቱ የተሳለጠ እንዲሆን ባለሙያዎችን አሰማርቶ በልዩ ሁኔታ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.