Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ለጂቡቲ ገበያ ለማቅረብ ስምምነት ተደረሰ

 አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ አዳዲስ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለጂቡቲ ገበያ ለማቅረብ ተስማሙ፡፡ የመጀመሪያው የኢትዮ-ጅቡቲ የአትክልትና ፍራፍሬ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በወቅቱም በርካታ የኢትዮጵያ ፍራፍሬና አትክልት ላኪዎች ከ20 በላይ ጥራት ያላቸውን ምርቶች ለዋና ዋና የጅቡቲ ገበያዎች ለማቅረብ ተስማምተዋል።
በኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራች ላኪዎች ማኅበር የተዘጋጀው የቢዝነስ ለቢዝነስ ውይይት ክፍተቶችን ለመገምገም እና ወደ ጅቡቲ የሚላኩ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለማሻሻል ጠቃሚ መድረክ ሆኖ አገልግሏል ነው የተባለው።
በውይይት መድረኩ ከኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራች ላኪዎች ማህበር ወደ ጅቡቲ የሚላከውን ምርት ለማሳደግ የሚያስችሉ አሰራሮችን በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በመድረኩ በተለይ አሁን ባለው የአለም የምግብ ቀውስ ወቅት ቀጠናዊ የንግድ ትስስርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
የጅቡቲ የልዑካን ቡድን በመጪዎቹ በቅርቡ በቢሾፍቱ እና በቆቃ እርሻዎችን ጉብኝት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ! ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.