Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና እና ኢኳቶሪያል ጊኒ በማዕድንና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና እና ኢኳቶሪያል ጊኒ በማዕድንና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት መካሄዱን የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለፁ ፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ከኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ጋር በመሆን ከኢኳቶሪያል ጊኒ የማዕድንና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር ጋር በማዕድን ኢንቨስትመንትና ንግድ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

ሁለቱ አገራት በማዕድንና ኢንቨስትመንት ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገናል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.