Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር መለስ ዓለም በኬንያ ከተባበሩት መንግስታት ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ጥር 26፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በኬንያ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ዛይነብ ሃዋ ባንጉራ ጋር መወያየታቸውን ገለጹ፡፡
አምባሳደር መለስ ዓለም፥ በኢትዮጵያ እና በቀጣናው እየተተገበሩ ባሉ የልማት ሥራዎች ላይ መምከራቸውን አመላክተዋል፡፡
በኢትዮጵያ በሰሜን የሀገሪቷ ክፍል አሸባሪው የህወሓት ቡድን ያደረሰውን ውድመት እና መንግስት ማኅበረሰቡን መልሶ ለማቋቋም እና ግንባታ የወሰዳቸውን እርምጃዎች ለዋና ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።
በተጨማሪም መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ሰብዓዊ እርዳታ በተሻለ ሁኔታ እንዲቀርብ እና ብሔራዊ መግባባት ላይ እንዲደረስ አካታች ውይይት እንዲጀመር እየሠራ መሆኑንም ማስረዳታቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡
ኢትዮጵያ በሱዳን አዋሳኝ ድንበር የተፈጠሩትን ግጭቶች እና በታላቁ ኅዳሴ ግድብ ላይ የሚነሱትን ሃሳቦች ከሀገራቱ ጋር በሁለትዮሽ ወይም ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን ባሳተፈ እና ሁሉንም ወገን አሸናፊ በሚያደርግ ውይይት ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
አምባሳደሩ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የአሸባሪውን የህወሓት ቡድን ግፍ በአንድ ድምጽ እንዲያወግዝ እና ከኢትዮጵያ መንግስት ጎን እንዲቆም መጠየቃቸውንም በመረጃቸው አመልክተዋል፡፡
በኬንያ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዛይነብ ሃዋ ባንጉራ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወሳኝ አባል እንደሆነችና በቀጣይም ከመንግስት ጋር በቅርበት መሥራት እንደሚፈልጉ በኬንያ ከሚገኘው የኢትጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.