Fana: At a Speed of Life!

ባህርዳርን ከሩሲያ ከተሞች ጋር በእህትማማችነት ለማስተሳሰር በቅንጅት ይሰራል- አምባሳደር ኢቭጀኒ ተረኺን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳደር ኢቭጀኒ ተረኺን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በባህር ዳር ከተማ እድገትና መሰረተ ልማቶች እንዲሁም በከተሞች ትስስር ጉዳይ መክረዋል፡፡

አምባሳደር ኢቭጀኒ ተረኺን ለኢትዮጵያ ያላቸውን ፍቅርና አክብሮት እንዲሁም ለባህር ዳር ከተማ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

አምባሳደሩ ባህርዳር ከተማን ለሩሲያ ከተሞች የእህትማማችነት ትስስር እንደሚመርጧት እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በቅንጅት እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከባህር ዳር ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.