Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ በጤና ዘርፍ ባሉ ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ላይ ያተኮረ ፎረም በዱባይ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በፋርማሲዪቲካልና በጤና ዘርፎች ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን የሚያስተዋውቅ የኢንቨስትመንት ፎረም የውጭና የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች በተገኙበት በዱባይ ተካሄዷል።
በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ተወካይ አቶ አበበ መብራቱ÷ ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በንግድ በኢንቨስትመንት፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ዘርፎች ሰፊ ትብብርና ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባለሀብቶች በአገራችን የተሰማሩባቸውን የኢንቨስትመንት ዘርፎች በማስፋት በፋርማሲዪቲካልና በጤና ዘርፎች ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶች መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡
አቶ ሰንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ስራ አስፈጻሚ በበኩላቸው÷ በአገራችን በፋርማሲዪቲካልና በጤና እንዲሁም በኢንዱስትሪ ፓርኮች በተዘጋጁ ሼዶች የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባለሀብቶች፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮች ወዋዕለነዋያቸውን ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። ለዚህም ድጋፍና ማበረታቻ እንደሚደረግላቸው ማረጋገጣቸውን ከዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በፎረሙ ላይ የተለያዩ የኢትዮጵያ የስራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባለሀብቶች፣ የውጭ ኢንቨስተሮች እና የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ተሳትፈዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.