በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ መካከል ያለው የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እየጎለበተ መምጣቱ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ መካከል ያለው የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት እያደገ መምጣቱን በኢትዮጵያ የኢንዶኔዥያ አምባሳደር ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ የኢንዶኔዥያ አምባሳደር አል ቡስይራ ባስኑር ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፤ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሁሉም መስክ እያደገ መጥቷል።
///የአገራቱ ግንኙነት በተለይ በኢኮኖሚ ዘርፍ እየጠነከረ መምጣቱን ጠቅሰው ባለፈው ዓመት 70 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያለው የንግድ ልውጥ መደረጉን ገልጸዋል።
በሁለቱ አገራት መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት ይበልጥ እንዲጎለብት የንግድ ትብብሩን የማጠናከር ስራ ይሰራል ብለዋል።
እንደ አምባሳደሩ ገለጻ በርካታ የኢንዶኔዥያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታ መኖሩ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
80 በመቶ የኢንዶኔዥያ ዲፕሎማሲ የሚያተኩረው ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
ኢንዶኔዥያ ጥጥ፣ ቆዳ፣ ቅመማ ቅመሞችንና ቡናን በስፋት ከኢትዮጵያ እንደምትሸምት አምባሳደር አል ቡስይራ አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ ደግሞ ዘይት፣ ሳሙና፣ ወረቀት፣ የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶችን እንዲሁም የቤተ ውበት እቃዎችን ከኢንዶኔዥያ እያሰገባች ትገኛለች ነው ያሉት፡፡
በትምህርት ዘርፍም ቢሆን በርካታ የኢንዶኔዥያ ዩኒቨርሲቲዎች ከኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተባብረው መስራት እንደሚፈልጉም ጨምረው ገልጸዋል።
እስካሁንም አርባ ምንጭ፣ ባህር ዳር፣ ሐዋሳና ኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ከኢንዶኔዥያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር አብረው መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸውን አንስተዋል።
በኢትዮጵያና በኢንዶኔዥያ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመረው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1961 ዓ.ም መሆኑን የታሪክ ድርሳናት ያመላክታሉ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!