Fana: At a Speed of Life!

በተባበሩት መንግስታት የፀረ-ሙስና ጉባኤ የኢትዮጵያ አፈፃፀም ግምገማ ሪፖርት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ዙር የተባበሩት መንግስታት የፀረ-ሙስና ጉባኤ የኢትዮጵያ አፈፃፀም ግምገማ ረቂቅ ሪፖርት ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት እየተካሄደበት ነው፡፡
በጉባኤው ምዕራፍ ሁለት ሙስናን መከላከልና በምዕራፍ አምስት የተመዘበረ ሀብትን ማስመለስ ላይ ትኩረቱን ባደረገው ሪፖርት ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ከፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የብሔራዊ የቴክኒክ ገምጋሚ ኮሚቴ አባል በመሆን÷ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን፣ ፍትህ ሚኒስቴር፣ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ብሔራዊ ባንክ፣ ፋይናንስና መረጃ ደህንነት አገልግሎት፣ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ ፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን እና የመንግስት ግዥ አገልግሎት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.