Fana: At a Speed of Life!

በሽብርተኛው ህወሃት ጥቃት የደረሰባቸዉ የሰሜን ሸዋ አካባቢዎችና አጎራባች ወረዳዎች አሁን ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ተመልሰዋል

አዲስ አበባ፣የካቲት 18፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህወሀት የሽብር ቡድን ወረራ ወቅት በሰሜን ሸዋ ዞን ጥቃት የደረሰባቸዉ አካባቢዎች እና አጎራባች ወረዳዎች አሁን ወደመደበኛ እንቅስቃሴያቸው ተመልሰዋል ።

በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል የነበረውን ጦርነት ወደመሀል ሀገር የመግፋት እንቅስቃሴ ስልት የነበረዉ የሽብር ቡድኑ ህወሀት እንቅስቃሴ ከወራት በፊት ማክተሙን ተከትሎ የሽብር ቡድኑ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ከተሞች መደበኛ እንቅስቃሴን ጀምረዋል፡፡

እንደ ደብረ ብርሀን ያሉ ከተሞችም ኢንቨስትመንትን የመሳብ የቀደመ እንቅስቃሴያቸውን መቀጠላቸዉን በአካባቢዎቹ ቅኝት ያደረገዉ ፋና ብሮድካስቲንገው ኮርፖሬት አረጋግጧል ።

ህወሀት የሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል ቀውስ ወደመሀል ሀገር ለመሳብ ባደረገዉ እንቅስቃሴ የሰሜን ሸዋ ዞን 7 ወረዳዎች ላይ ጥቃት የፈፀመ ሲሆን÷ በወረዳዎቹ የሚገኙ ከ94 በላይ የኢንደስትሪ እና የኢንቨስትመንት መሰረተ ልማቶች ላይ ከ454 ሚሊየን 788 ሺህ ብር ግምት ያለው ንብረት ላይ ጥፋት አድርሷል ።

የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ አቶ ካሳሁን እምቢ አለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ ”ከተማዋ በርካታ የኢንቨስትመንት እድልና አማራጭ ያላት ፣ ለኢንዱስትሪም የተመቸች ናትና ከተማዋን ከወትሮ በተለየ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል ።

ጦርነቱ የፈጠረው ኢንቨስትመንቱን የማቀዝቀዝ አይነት ተፅእኖዎች ነበሩ ያሉት ከንቲባው፥ አሁን ግን በሁሉም ዘርፍ ያሉትን የኢንቨስትመንት ጥያቄ ያላቸዉን አካላት በልዩ ሁኔታ እያስተናገድን ነው ብለዋል ።

በፀጋዬ ወንደሰን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.