Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ተጋጣሚያቸውን ረቱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ10ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ወልቂጤ ከተማን እንዲሁም ወላይታ ድቻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸንፈዋል፡፡ 9፡00 ሠዓት ላይ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጌታነህ ከበደ ከመረብ ባገናኛት ብቸኛ ጎል ፋሲል ከነማ ወልቂጤ ከተማን አሸንፏል፡፡ ዐፄዎቹ 1 ለ0 ማሸነፋቸውን ተከትሎም በ18 ነጥብ 5 ደረጃን ሲይዙ፤ ወልቂጤ ከተማ በ8 ነጥብ 14 ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም 12፡00 ሠዓት ላይ በተካሄደ ሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር ወላይታ ድቻ…
Read More...

የ2023 አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ኮትዲቯር

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2023 አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኮትዲቯር ዝግጅቷን አጠናቃ እንግዶቿን እየተቀበለች ነው። የውድድሩ ተሳታፊ ሀገሮች ኮትዲቯር ገብተው የውድድሩን መጀመር በመጠባበቅ ላይ ናቸው። የዘንድሮሮውን አህጉራዊ ውድድር ያዘጋጀችው ኮትዲቯር በፈረንጆቹ መስከረም 2002 የተከሰተው ወታደራዊ አመፅ ብዙ ሰብዓዊ እና…

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ የአሜሪካ የ2023 የምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሳን ዲያጎ ዌቭ የሴቶች ቡድን እየተጫወተች የምትገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ የአሜሪካ የ2023 የሴቶች ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፋለች፡፡ በዚህም የ23 አመቷ ናኦሚ በአሜሪካ ሴቶች እግርኳስ ታሪክ የመጀመሪያዋ ተከላካይ እና ሁለተኛዋ ጥቁር የአመቱ ምርጥ ሴት ተጫዋች ሽልማት አሸናፊ መሆን ችላለች፡፡ ናኦሚ…

በፕሪሚየር ሊጉ ድሬደዋ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት የውድድር መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ ድሬደዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ያካሄዱት ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡ የድሬደዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቻርለስ ሙሰጌና ካርሎስ ዳምጠው ሲያስቀጥሩ÷የኢትዮጵያ መድንን ብቸኛ ግብ ደግሞ ወገኔ…

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥብ ጣለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው 10ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ተለያይቷል፡፡ 9፡00 ላይ ሐዋሳ ከተማን የገጠመው መቻል 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ የመቻልን ጎሎችም ምንይሉ ወንድሙ እና ከንዓን ማርክነህ ሲያስቆጥሩ÷ የሐዋሳ ከተማን ብቸኛ ጎል አሊ ሱለይማን…

 ለአፍሪካ ዋንጫ የተለያዩ ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች አቢጃን እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚደረገው የ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የተለያዩ ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች ወደ አቢጃን እየገቡ ይገኛሉ፡፡ ትናንት ምሽት የካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን  የሴኔጋል  ብሄራዊ ቡድን ኮትዲቯር የገባ ሲሆን÷ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ከልዑካን ቡድኑ ጋር አቢጃን ገብተዋል፡፡ የካሜሮኑ የአፍሪካ…

የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት የውድድር መርሐ ግብር የመጀመሪያ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ ሻሸመኔ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ያካሄዱት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡ የሻሸመኔ ከተማን ግብ አብዱልቃድር ናስር ሲያስቆጥር÷ኢትዮጵያ ቡናን አቻ ያደረገችዋን ግብ ደግሞ…