Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የሐዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ፖሊዮን ጨርሰን እናጥፋ” በሚል መሪ ሐሳብ የ2016 ሐዋሳ ሐይቅ ግማሽ ማራቶን ውድድር ለ12ኛ ጊዜ ተካሂዷል። በስድስት የውድድር ዘርፎች 150 አትሌቶችን ጨምሮ ከ4 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች በውድድሩ ተሳትፈዋል፡፡ በ21 ኪሎ ሜትር የተካሄደውን የወንዶች ውድድር እንየው ንጋት በግል 1 ሠዓት ከ2 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል፡፡ እንዲሁም አሰፋ ተፈራ 1 ሠዓት ከ2 ከ47 ሰከንድ በመግባት 2ኛ፤ ደበበ ተካ ደግሞ 1 ሠዓት ከ3 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን…
Read More...

የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮትዲቯር አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል፡፡ በማጠቃለያ መርሐ-ግብሩም ናይጄሪያ ከኮትዲቯር ለፍጻሜ የሚያደርጉት ጨዋታ አጓጊ ሆኗል፡፡ ጨዋታው ምሽት 5፡00 ሠዓት ላይ 60 ሺህ ተመላክቾችን የማስተናገድ አቅም ባለው ኦሊሳን ኦታራ ስታዲየም ይደረጋል። ከፍጻሜው ጨዋታ…

የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ዛሬ የተካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቅቀዋል፡፡ ቀን 9 ሰዓት አዳማ ከተማ ከፋሲል ከነማ ያደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡ የፋሲል ከነማን ብቸኛ ግብ ጌታነህ ከበደ ሲያስቆጥር÷ሲቦና ዓሊ ደግሞ ለአዳማ ከተማ አስቆጥሯል፡፡ ምሽት…

አቶ ኢሳያስ ጅራ የካፍ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ካፍ ባደረገው ስብሰባ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አድርጎ መምረጡን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡…

በፕሪሚየር ሊጉ ባህርዳር ከነማ 4ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚርሊግ ባህርዳር ከተማ 4ኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡ ቀን 9 ሰዓት ላይ ሀድያ ሆሳዕናን የገጠመው የአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ቡድን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎም የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ የነበረው ባህርዳር ከተማ የውጤት ቀውስ ውስጥ ገብቷል፡፡…

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት በተካሄደው 14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና እና ሲዳማ ቡና ድል ቀንቷቸዋል፡፡ 9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ጎሎች በዛብህ መለዮ እና…

የጃፓኗ ካሳማ ከተማ ከንቲባ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስፖርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓኗ ካሳማ ከተማ ከንቲባ ሺንጁ ያማጉቺ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተለያዩ የስፖርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል። በጃፓን ካሳማ ከተማ ላለፋት ተከታታይ አምስት ዓመታት በታሕሳስ ወር በጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ በቂላ ለመዘከር የግማሽ ማራቶን ውድድር ይዘጋጃል ተብሏል፡፡ ከንቲባ ሺንጁ ያማጉቺ ዛሬ ለኢትዮጵያ…