ስፓርት
ቶማስ ቱኸል በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሙኒክ ጋር ይለያያሉ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከባየርን ሙኒክ ጋር እንዲለያዩ መወሰኑን ክለቡ አስታወቀ፡፡
አሰልጣኙ አንድ ዓመት የኮንትራት ጊዜ ቢኖራቸውም የክለቡ አመራሮች በክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከመከሩ በኋላ የውድድር ዓመቱ ሲጠናቀቅ እንዲለቁ ወስነዋል፡፡
ውሳኔው የተላለፈውም ባየርንሙኒክ ከ12 ዓመታት በኋላ ባጋጠው ተደጋጋሚ ሽንፈት ምክንያት ከዲ ኤፍ ቢ ፖካል ዋንጫ ውጪ መሆኑን እና ከቡንደስ ሊጋው ፉክክርም ከመሪው በ8 ነጥብ ልዩነት ተበልጦ መቀመጡን ተከትሎ ነው…
Read More...
ምባፔ በክረምት የዝውውር መስኮት ማድሪድን ለመቀላቀል ተስማማ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓሪሴንት ዥርሜይ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል ተስማምቷል፡፡
የ25 ዓመቱ ፈረንሳዊ ምባፔ÷ ሪያል ማድሪድ እና ፒ ኤስ ጂ በሻምፒዮንስ ሊጉ የማይገኛኙ ከሆነ በቅርቡ ለማድሪድ የኮንትራት ፊርማውን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡
ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫን…
አቡበከር ናስር ካጋጠመው ጉዳት አገግሞ ወደ ሜዳ እንዲመለስ ድጋፋችን ያስፈልገዋል – አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አቡበከር ናስር ካጋጠመው ጉዳት አገግሞ ወደ ሜዳ እንዲመለስ ድጋፋችን ያስፈልገዋል ሲሉ የማሜሎዲ ሰንዳውንስ አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ገለፁ፡፡
አሰልጣኙ የአጥቂ መስመር ተጫዋቹን አቡበከርን አስመልከተው በሰጡት አስተያየት÷ አቡበከር ከኦርላንዶ ፓይሬትስ ጋር በነበረው ጨዋታ ያጋጠመው ጉዳት ከባድ መሆኑን አንስተዋል።…
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዋንጫ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ፡፡
የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን የሚያሳትፈው የድሬ ዋንጫ ከየካቲት 16 ጀምሮ በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ይደረጋል።
በውድድሩ ለሚሳተፉና ጥሪ የተደረገላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችም ከየካቲት 13 ጀምሮ በተዘጋጀላቸው ሆቴል…
የሀሪ ኬን የዋንጫ እርግማን
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቶተንሃም እና የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን የምንጊዜም ጎል አስቆጣሪው ሃሪ ኬን ከአዲሱ ትውልድ ምርጥ አጥቂዎች ውስጥ ስሙ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡
በእግር ኳስ ሜዳ ላይ የጎላ አስተዋጽኦ ቢያደርግም ዋንጫ አንስቶ በመሳም ረገድ ግን ዕድል ከእሱ ጋር አይደለችም።
የ30 ዓመቱ አጥቂ በክለብ እና በብሄራዊ ቡድን ባደረጋቸው…
በፕሪሚየር ሊጉ አርሰናል እና ሊቨርፑል ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል እና ሊቨርፑል ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ሊቨርፑል ከብሬንትፎርድ ጋር ባደረገው ጨዋታ 4 ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል፡፡
በሌላ በኩል አርሰናል በርንሌይን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ÷ወልቭስ ደግሞ ቶተንሃምን 2 ለ1 አሸንፏል፡፡
በተመሳሳይ…
በጋምቤላ ክልል አቀፍ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው የመላ ጋምቤላ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር በጋምቤላ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።
ውድድሩን ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ እንዳሉት÷ ስፖርት የህዝቦችን አንድነት በማጠናከር ረገድ የጎላ ፋይዳ ስላለው ውድድሩን በጨዋነት ማካሄድ ይገባል።
በመሆኑም ውድድሩ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ፍፃሜውን እንዲያገኝ…