Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ 15ኛውን የመላው አፍሪካ ጨዋታ የማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የ2031ን 15ኛውን የመላው አፍሪካ ጨዋታ የማዘጋጀት ፍላጎት እንዳላት ገለፀች፡፡ ኢትዮጵያ ፍላጎቷን የገለፀችው ከ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታ ጎንለጎን በተካሄደ የአፍሪካ ጨዋታዎች ቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ ከትናንትና በስቲያ የተከፈተው እና እስከ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ በጋና አክራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በዚህ ጨዋታ ላይ 54 የአፍሪካ ሀገራት በ29 የስፖርት አይነቶች የሚሳተፉ ሲሆን ÷ኢትዮጵያም በዘጠኝ የስፖርት አይነቶች…
Read More...

ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ መድንን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ 10፡00 ሠዓት ላይ በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የፋሲል ከነማን የድል ጎሎች ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት እና ናትናኤል ማስረሻ በጨዋታ አስቆጥረዋል፡፡ ውጤቱን ተክትሎም አፄዎቹ ነጥባቸውን ወደ 29 ከፍ…

ማንቼስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡ የዩናይትድን የማሸነፊያ ጎሎች ማርከስ ራሽፎርድ እና ቡሩኖ ፈርናንዴዝ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል፡፡ ሁለቱም የፍፁም ቅጣት ምቶች በአርጀንቲናዊው የመስመር አጥቂ ጋርናቾ የተገኙ ሲሆን÷ በውድድር ዓመቱም ለክለቡ ሁለት ፍፁም…

13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) እስከ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆየው 13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታ በጋና አክራ በይፋ ተከፍቷል፡፡ በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ÷ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት፣ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽነሮች፣ የጋና ፕሬዚዳንት ናና አኩፋ ዶን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶችና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል፡፡ ውድድሩን…

የሜሲን ስም በመጥራት ከሃማስ እገታ የተረፉት የ90 ዓመት አዛውንት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ90 ዓመቷ አዛውንት የሊዮኔል ሜሲን ስም በመጥራት ከሃማስ እገታ መትረፋቸው መሰማቱ አነጋጋሪ ሆኗል። ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት በፈፀመበት በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 ቀን 2023 ዕለት ነገሩ የተፈጸመው። በዕድሜ የገፉት የ90 ዓመቷ አዛውንት ኤስተር ኩኒዮ ቤታቸው ውስጥ ከተቀመጡበት የሃማስ አጋቾች በድንገት ይገቡና…

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ትዕግስት አሰፋ በለንደን ማራቶን ይሳተፋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና የወቅቱ የሴቶች ማራቶን ክበረ ወሰን ባለቤት ትዕግስት አሰፋ በ2024 የለንደን ማራቶን ውድድር እንደሚሳተፉ የለንደን ማራቶን አዘጋጅ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ የ41 ዓመቱ አትሌት ቀነኒሳ በ2023ቱ የቫሌንሲያ ማራቶን 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ9 ሰከንድ በመግባት በአንጋፋ ዕድሜ ዘርፍ አዲስ ክብረወሰን…

በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስኮትላንድ ግላስኮው በተካሄደው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በአፍሪካ ቀዳሚ ሆኖ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ። የባህልና የስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ…