ስፓርት
ኖቲንግሃም ፎረስት 4 ነጥብ ተቀነሰበት
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኖቲንግሃም ፎረስት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የፋይናንሺያል ጨዋነት ሕግ ተላልፏል በሚል አራት ነጥብ ተቀነሰበት፡፡
ቡድኑ ሕጉን በመተላለፍ ፕሪሚየር ሊጉ ትርፋማ እንዳይሆን ማድረጉም በገለልተኛ አጣሪ ተረጋግጧል ነው የተባለው፡፡
ይህን ተከትሎም ቡድኑ አራት ነጥብ ተቀንሶበት ነጥቡ ከ25 ወደ 21 ዝቅ ብሏል፡፡
ኖቲንግሃም ፎረስት ከኤቨርተን በመቀጠል በውድድር ዓመቱ በፋይናንሺያል ጨዋነት ሕግ መተላለፍ ምክንያት ቅጣት የተጣለበት ቡድን ሆኗል፡፡
Read More...
በቱርክ እግር ኳስ የሚስተዋሉ የሜዳ ላይ እረብሻዎች…
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራብዞን ስፖርት ደጋፊዎች የፌነርባቼ ተጫዋቾችን በጨዋታው ማጠናቀቂያ መደባደባቸውን ተከትሎ የቱርክ ሱፐር ሊግ ሌላ አሳዛኝ ክስተት አስተናግዷል፡፡
ትላንት ምሽት በፓፓራ ፓርክ የተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ተመጣጣኝ ፉክክርን አስተናግዶ በፌነርባቼ 3 ለ 2 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡
በ87ኛው ደቂቃ ላይ የተለያዩ…
ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አስራ ስምንተኛ ሳምንት ጨዋታ በድሬዳዋ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
ፋሲል ከነማ እና ሲዳማ ቡና ቀን 10 ሰዓት ላይ ባደረጉት ጨዋታ 2 አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
በዚህም የፋሲል ከነማን ጎሎች…
አትሌት ጀማል ይመር የራሱን ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኮሪያ በተካሄደው የሴዑል ማራቶን አትሌት ጀማል ይመር የራሱን ፈጣን ሠዓት በማስመዝገብ አሸንፏል፡፡
አትሌት ጀማል ውድድሩን ያሸነፈው 2 ሰዓት ከ 6 ደቂቃ ከ8 ሰከንድ በመግባት ሲሆን÷ ይህም የግሉ ፈጣን ሠዓት ሆኖ ተመዝገቧል፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ 18ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በድሬዳዋ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
በዚሁ መሠረት 10:00 ሠዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከሲዳማ ቡና የሚጫወቱ ይሆናል፡፡
እንዲሁም 1:00 ሠዓት ላይ ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ መድን ጨዋታቸውን እንደሚደርጉ የወጣው መርሐ-ግብር ያመላክታል፡፡
ከ15 ሺህ ሴቶች በላይ የተሳተፉበት የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ15 ሺህ ሴቶች በላይ የተሳተፉበት 21ኛ ዙር ቅድሚያ ለሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
በውድድሩም ጉታኒ ሻንቆ 1ኛ፣ ብርነሽ ደሴ 2ኛ እና መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡
መነሻ እና መድረሻውን አትላስ ሆቴል አካባቢ ያደረገው የሩጫ ውድድር÷ “የሴቶችን አቅም…
በስፔን የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን ላሬዶ ከተማ በተካሄደ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል፡፡
አትሌት ዮሚፍ ርቀቱን 26 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡