Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ካፍ የአዲስ አበባ ስታዲየም እድሳት ላይ እንዲከናወኑ ያስቀመጣቸው ሥራዎች ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በአዲስ አበባ ስታዲየም እድሳት መመዘኛ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ እንዲከናወኑ ያስቀመጣቸው ሥራዎች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ። በሚኒስቴሩ የስፖርት ፋሲሊቲ ልማትና አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አስማረ ግዛው÷ ካፍ ባስቀመጠው መመዘኛ መሰረት የስታዲየሙ እድሳትና ጥገና ስራ መከናወን ከጀመረ ከ2 ዓመት በላይ ማስቆጠሩን አስታውሰዋል። በዚህም በመጀመሪያ ዙር እድሳት የስታዲየሙ የመጫወቻ ሜዳ፣ የተፈጥሮ ሳር ንጣፍ፣…
Read More...

በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያ የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ3 ሺህ ሜትር የሴቶች የመሰናክል ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት ሎሚ ሙለታ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ አትሌቷ 9 ደቂቃ 26 ሰከንድ ከ63 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው 3ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው፡፡ እንዲሁም አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ እና ፍሬሕይወት ገሰሰ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል፡፡…

በ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ውድድር ምስጋናው ዋቁማ 5ኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች በ20 ኪሎ ሜትር በተደረገ የወንዶች እርምጃ ውድድር ምስጋናው ዋቁማ 5ኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝቷል፡፡ በሴቶች 20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ደግሞ ስንታየሁ ማስሬ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ ለሀገሯ ማስገኘቷን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ናይጄሪያውያን ባለሃብቶች አውሮፓ ውስጥ የእግር ኳስ ክለብ ባለቤት መሆን ጀምረዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ናይጄሪያውያን ባለሀብቶች አንዳንዶቹ በአውሮፓ ውስጥ የእግር ኳስ ክለቦችን መግዛት በመጀመራቸው በዓላም ታሪክ ስማቸውን መፃፍ መቻላቸው ተነግሯል፡፡ ናጄሪያውያኑ በፖርቹጋል ሁለት የእግር ኳስ ቡድኖች ሲኖራቸው አንዱ ደግሞ በዴንማርክ አንድ ቡድን እንዳለው ይፋ የተደረጉ መረጃዎች አሳይተዋል፡፡ ናይጄሪያውያን የስፖርት…

በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 3ኛ ወርቋን አገኘች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በሴቶች 800 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያ 3ኛ ወርቋን በፅጌ ዱጉማ አማካኝነት አግኝታለች፡፡ ፅጌ ውድድሩን በ1 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ74 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ነው የጨረሰችው፡፡ ፅጌ ባለፈው ወር በተደረገው የአለም የቤት ውስጥ ውድድር የወርቅ ሜዳልያ ማሸነፏ ይታወሳል። ሌሎች…

ምሽት ላይ በሚከናወኑ ሁለት የፍጻሜ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት ላይ በሚካሄዱ የ800 ሜትር እና የ10 ሺህ ሜትር የፍጻሜ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተጠባቂ ናቸው፡፡ በዚሁ መሠረት የሴቶች 800 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ምሽት 4 ሠዓት ከ5 ደቂቃ ላይ የሚካሄድ ሲሆን÷ በዚሁ ዘርፍ አትሌት አስቴር አሬሬ እና ፅጌ ዱጉማ ይጠበቃሉ፡፡ እንዲሁም ምሽት 4 ሠዓት ከ35…

አትሌት ሳሙኤል ፍሬው በ3 ሺህ ሜትር መሰናከል የመጀመሪያውን ወርቅ ለሀገሩ አስገኘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ወንዶች አትሌት ሳሙኤል ፍሬው የመጀመሪያውን ወርቅ ለኢትዮጵያ አስገኝቷል፡፡ አትሌት ሳሙኤል ርቀቱን 8 ደቂቃ 24 ሰከንድ ከ30 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡ በመርሐ ግብሩ የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ውድድር ሲካሄድ ኢትዮጵያውያን…