ስፓርት
በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ በሚገኘው የቦክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካና ከሞሪሽየስ ጋር ትጋጠማለች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ በሚገኘው የማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን ቦክሰኞች በሁለቱም ፆታ ከደቡብ አፍሪካ እና ከሞሪሽየስ አቻቸው ጋር ይፋለማሉ፡፡
ምሽት 1 ሰዓት በደርባን ከተማ በሚደረገው ውድድር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቦክሰኞች የመጀመሪያ ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ያደርጋሉ፡፡
በወንዶች 57 ኪሎ ግራም አብዱሰላም አቡበከር ከደቡብ አፍሪካ አቻው ጋር የሚገጥም ሲሆን በ60 ኪሎ ግራም ደግሞ አቡበከር ሰፋን ከሞሪሽየስ አቻው ጋር የሚጋጠም ይሆናል፡፡
በ67 ኪሎ…
Read More...
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል ከባየርንሙኒክ እንዲሁም ማንቸስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ ዛሬ ምሽት 4:00 ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
ባየርንሙኒክ ከአርሰናል በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ በአርሰናል በኩል ማርቲን ኦዲጋርድ እና ቡካዮ ሳካ በጉዳት ምክንያት መሰለፋቸው…
ፕሪሚየር ሊጉ ከ23ኛ ሣምንት ጀምሮ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ‘በኢትዮጵያ ዋንጫ’ ጨዋታዎች ምክንያት ከተቋረጠ በኋላ ሲመለስ ከ23ኛ ሣምንት ጀምሮ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ16ኛ እስከ 22ኛ ሣምንት በድሬዳዋ ከተማ - ድሬዳዋ ስታዲየም እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ ‘በኢትዮጵያ…
የሻምፒዮንስ ሊጉ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ፡፡
ዛሬ ምሽት ከሚደረጉት መርሐ ግብሮች ባርሴሎና በሜዳው ኑ ካምፕ የፈረንሳዩን ፓሪስ ሴንት ዠርሜይንን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃሉ፡፡
ባለፈው ሳምንት ሁለቱ ቡድኖች በፓሪስ ፓርክ ዴስ ፕሪንስ ባደረጉት ጨዋታ ባርሴሎና 3ለ2…
አትሌት ሲሳይ ለማ በቦስተን ማራቶን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ቦስተን ማራቶን አትሌት ሲሳይ ለማ አሸንፏል፡፡
አትሌት ሲሳይ ርቀቱን 2 ሰዓት 6 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ያሸነፈው፡፡
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት መሃመድ ኢሳ ደግሞ ውድድሩን ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቅቋል፡፡
በሮተርዳም ማራቶን አትሌት አሼቴ በከሪ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኔዘርላንድስ ሮተርዳም ማራቶን አትሌት አሼቴ በከሪ አሸንፋለች፡፡
አትሌቷ 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ30 ሴኮንድ በመግባት ነው ውድድሩን ቀዳሚ ሆና ያጠናቀቀችው፡፡
ኬንያውያኖቹ ቮይላ ኪቢዮት እና ሴሊ ኪፔይጎ ሁለተኛ እና ሶሰተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡
በወንዶች ደግሞ አምደወርቅ ዋለልኝ 2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ…
ማንቸስትር ሲቲና ኒውካስል ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ማንቸስተር ዩናይትድ አቻ ተለያይቷል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 33ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ማንቸስትር ሲቲና ኒውካስል ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን በሰፊ የጎል ልዩነት ሲያሸንፉ ማንቸስተር ዩናይትድ አቻ ተለያይቷል፡፡
ሉተን ተዎንን በሜዳው ያስተናገደው ማንቸስትር ሲቲ 5 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ኒውካስል ዩናይትድ በበኩሉ ቶተንሃም ሆትስፐርን 4 ለ 0…