ስፓርት
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በነገው የለንደን ማራቶን ላይ ይወዳደራሉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለማችን ታዋቂ አትሌቶች የሚሳተፉበት የ2024 የለንደን ማራቶን በነገው ዕለት ይካሄዳል፡፡
በውድድሩ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን÷ በወንዶች አትሌት ቀነኒሳ በቀለ፣ ሞስነት ገረመውና ታምራት ቶላ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷቸዋል።
በሴቶች ደግሞ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው፣ ትዕግስት አሰፋና አልማዝ አያና ውድድሩን በአሸናፊነት ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ውድድሩን በአንደኝነት የሚያጠናቅቁ የ55 ሺህ ዶላር፣ ሁለተኛ የሚወጡት የ30 ሺህ ዶላር ሶስተኛ ሆነው…
Read More...
አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ1 ሺህ 500 ሜትር በታሪክ ሶስተኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ1 ሺህ 500 ሜትር ርቀት በታሪክ ሶስተኛውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸነፈች።
በቻይና ዝያሜን እየተካሄደ ባለው ዲያመንድ ሊግ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3:50.30 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀች ሲሆን፤ የገባችበት ሰዓት በርቀቱ በታሪክ ሶስተኛው ፈጣን ሰዓት መሆኑን የዓለም…
አትሌት ለሜቻ ግርማ በቻይና በተካሄደ 5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ በቻይና ዢያሜን በተካሄደ የዲያመንድ ሊግ 5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸነፈ።
12:58.96 በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው አትሌት ለሜቻ ግርማ፤ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል በርካታ ድል በማስመዝገብ የሚታወቅ አትሌት ነው።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው 22ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ ሀምበሪቾን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ቀን 10፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሀዋሳ ከተማን ለድል ያበቃውን ጎል የሀምበሪቾው ዲንክ ኪያር በራሱ ላይ አስቆጥሯል።
በተመሳሳይ ቀን 1:00 ላይ የተካሄደው የፋሲል ከነማ እና የአዳማ ከተማ…
በማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ ሚሊዮን ጨፎ የደቡብ አፍሪካ አቻዋን በበቃኝ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ እየተካሄደ ባለው የማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ሚሊዮን ጨፎ የደቡብ አፍሪካ አቻዋን በበቃኝ አሸንፋለች፡፡
በ60 ኪሎግራም የደቡብ አፍሪካ አቻዋን የገጠመችው ቦክሰኛዋ በውድድሩ ሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ባሰረፈችው ቡጢ በዳኛ ውሳኔ አማካኝነት በበቃኝ ማሸነፍ ችላለች።…
በማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ም/ሳጅን ሮማን አሰፋ ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የማንዴላ መታሰቢያ ዋንጫ የቦክስ ውድድር ምክትል ሳጅን ሮማን አሰፋ ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች፡፡
ትናንት ምሽት ሀገሯን የወከለችው የአዲስ አበባ ፖሊሷ ምክትል ሳጅን ሮማን አሰፋ በ54 ኪሎ ግራም የናሚቢያ ተጋጣሚዋን በመጀመሪያው ዙር በበቃኝ…
ቤተልሔም ወልዴ በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ሻምፒዮና ተጋጣሚዋን በበቃኝ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማንዴላ አፍሪካን ቦክሲንግ ካፕ ሻምፒዮና ከደቡብ አፍሪካ አቻዋ ጋር የተጋጠመችው ቤተልሄም ወልዴ በበቃኝ አሸንፋለች፡፡
የመላው አፍሪካ ሻምፒዮኗ ቤተልሄም ወልዴ በሁለተኛ ዙር ላይ ተጋጣሚዋ ላይ ሀይለኛ ቡጢ በማሳረፍ ነው በዳኛ ውሳኔ ያሸነፈችው፡፡
በወንዶች ምድብ ኢትዮጵያን የወከሉት አቡዱሰላም አቡበከር፣ አቡበከር…