Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ባሕር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና ይገናኛሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት ባሕር ዳር ከተማ ከሲዳማ ቡና 10 ሠዓት ላይ እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከወዎላይታ ድቻ 1 ሠዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የወጣው መርሐ-ግብር አመላክቷል፡፡
Read More...

ማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ፡፡ በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት አሰልጣኝ ቴን ሃግ ስኬታማ ጉዞ እያደረጉ አይደለም በሚል ትችት ሲሠነዘርባቸው ቆይቷል፡፡ ቀያይ ሰይጣኖቹ ትናንት ባደረጉት የፕሪሚየር ሊጉ ዘጠነኛ ሣምንት ጨዋታ በዌስት ሃም 2 ለ 1 መሸነፋቸው ይታወሳል፡፡ በክለቡ…

4 ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ዕጩ ውስጥ ተካተቱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ታምራት ቶላ፣ ትዕግስት ከተማ እና ሱቱሜ አሰፋ የ2024 ከስታዲየም ውጭ የወንዶች የዓመቱ ምርጥ አትሌት ምርጫ ላይ በዕጩነት ተካተቱ፡፡ አትሌቶቹ በውድድር ዓመቱ በተለያዩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ባስመዘገቡት ውጤት ነው ለዕጩነት መካተት የቻሉት። በውድድር ዓመቱ አትሌት ታምራት ቶላ…

አርሰናል እና ሊቨርፑል አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሣምንት ጨዋታ በሜዳው ሊቨርፑልን ያስተናገደው አርሰናል 2 አቻ ተለያይቷል። 1 ሠዓት ከ30 ላይ በተካሄደው ጨዋታ፥ ቡካዮ ሳካ እና ሚኬል ሜሪኖ የመድፈኞቹን ግቦች አስቆጥረዋል። ቨርጅል ቫን ዳይክ እና ሞሐመድ ሳላህ ደግሞ የሊቨርፑልን ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።…

ቼልሲ ሲያሸንፍ ማንቼስተር ዩናይትድ ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ፣ ክሪስታል ፓላስ እና ዌስትሃም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ ቼልሲ ከኒውካስል ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 1 ሲያሸንፍ ግቦቹን ጃክሰን እና ፓልመር አስቆጥረዋል፡፡ የኒውካስልን ብቸኛ ግብ ደግሞ ኢሳቅ አስቆጥሯል፡፡ ክሪስታልፓላስ ቶተንሃምን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ግቧን ማቴታ አስቆጥሯል፡፡…

በፍራንክፈርት ማራቶን አትሌት ሀዊ ፈይሳ ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን ፍራንክፈርት በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ውድድር  አትሌት ሀዊ ፈይሳ ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች። አትሌት ሀዊ ፈይሳ ውድድሩን  2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ በመግባት ማሸነፏን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ የዓለም የግማሽ ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በቫሌንሺያ ሜዲዮ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር የዓለም ክብረወሰንን በመስበር ጭምር አሸነፈ፡፡ አትሌቱ ርቀቱን ያጠናቀቀው 57 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ በመግባት መሆኑን የዓለም አትሌቲክስ መረጃ አመላክቷል፡፡ የዓለም የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን በዑጋንዳዊው አትሌት  ጃኮብ ኪፕሊሞ ተይዞ መቆየቱ…