ስፓርት
በፓሪስ ኦሊምፒክ ዳያስፖራዎች በውድድሩ ቦታ ተገኝተው አትሌቶችን እንዲያበረታቱ ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ ከ200 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች በውድድር ስፍራ ተገኝተው አትሌቶችን እንዲያበረታቱ እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ።
በፓሪስ ኦሊምፒክ ውጤታማ ለመሆን የሚያስችል ጠንካራ ስራ እየተሰራ እንደሆነ የፓሪስ ኦሎምፒክ የብሔራዊ ዝግጅት ኮሚቴ አስታውቋል።
ኮሚቴው በተሰጠ መግለጫ፤ ኢትዮጵያን የሚመጥን ውጤት ለማስመዝገብ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጿል።
የኮሚቴው ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፤ በውድድሩ ከ200 ሺህ በላይ ዳያስፖራዎች በስፍራው ተገኝተው…
Read More...
ቼልሲ ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቸቲኖን በጋራ ስምምነት ከአሰልጣኝነት አሰናበተ፡፡
የ52 ዓመቱ ፖቸቲኖን እንደ አውሮፕያኑ አቆጣጠር ሐምሌ 1 ቀን 2023 ነበር ቼልሲን ለማሰልጠን የሁለት ዓመት ኮንትራት የተፈራረሙት፡፡
ቼልሲ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በ6ኛ ደረጃ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
ቶኒ ክሩስ ከዩሮ 2024 በኋላ ጫማ እንደሚሰቅል አስታውቋል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሪያል ማድሪድ እና የጀርመኑ አማካኝ ቶኒ ክሩስ በቀጣይ ወር ሀገሩ ከምታስተናግደው ዩሮ 2024 መጠናቀቅ በኋላ ጫማ እንደሚሰቅል አስታውቋል፡፡
በፈረንጆቹ ጥር 4/1990 በምስራቅ ጀርመን የተወለደው ክሩስ የፕሮፌሽናል እግርኳስ ህይወቱን የጀመረው በባየር ሙኒክ ሲሆን ሶስት የቡንደስሊጋ እና ሶስት የጀርመን ጥሎ ማለፍ…
ማንቼስተር ሲቲ የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ሲቲ ብርቱ ፉክክር በታየበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ሆኗል፡፡
በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን ባገኘው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ዌስትሃምን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ 3 ለ1 ማሸነፉን ተከትሎ ነው ሻምፒዮንነቱን ያረጋገጠው፡፡
በዚህም 91 ነጥቦችን በመሰብሰብ ፕሪሚየር…
የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምሽቱን ፍጻሜውን ያገኛል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን ዛሬ በተመሳሳይ አመሻሽ 12:00 ላይ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጠናቀቃል።
የሊጉ መሪ ማንቼስተር ሲቲ እና ተከታዩ አርሰናል ዋንጫውን የማሸነፍ ዕድል ይዘው በሜዳቸው ተጋጣሚዎቻቸውን ያስተናግዳሉ።
ማንቼስተር ሲቲዎች በኢቲሃድ ከዌስትሃም ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ በድል…
በፕሪሚየር ሊጉ አዳማ ከተማ ተጋጣሚውን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ25ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዳማ ከተማ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 1 ረትቷል፡፡
በጨዋታውም መስዑድ መሐመድ እና ቢንያም አይተን ለአዳማ ከተማ እንዲሁም ደስታ ዮሐንስ ለሲዳማ ቡና ጎሎቹን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል፡፡
እንዲሁም 12 ሠዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ሻሸመኔ ከተማን ኢትዮጵያ ቡና 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡…
ኢትዮጵያ 3ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍ የቡድኑ አባል የነበሩት ኃ/ማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ1954 ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋች የነበሩት ኃይለማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
በቅፅል ስማቸው "ሻሾ" በሚል በስፖርት ቤተሰቡ በስፋት የሚታወቁት ኃይለማርያም መኮንን÷ ከ1940ዎቹ መጨረሻ እስከ 60ዎቹ መጀመሪያ በነበረው የተጫዋችነት ሕይወታቸው ለጥቅምት 23፣ ሸዋ…