Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሉካ ሞድሪች ለተጨማሪ አንድ ዓመት ውሉን አራዘመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሪያል ማድሪዱ አማካይ ሉካ ሞድሪች በሳንትያጎ ቤርናቢዩ ለተጨማሪ አንድ ዓመት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል፡፡ በፈረንጆቹ 2012 ከእንግሊዙ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ሪያል ማድሪድን የተቀላቀለው የ38 ዓመቱ ክሮሺያዊው አማካይ ሉካ ሞድሪች፤ ለ12 የውድድር ዓመታት የሎስ ብላንኮዎቹ የቡድን ድምቀት መሆን ችሏል፡፡ በቆይታው ከስፔኑ ሀያል ክለብ ጋር 6 የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ፣ 5 የክለቦች የዓለም ዋንጫ፣ 4 የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ዋንጫ፣ 4 የላ ሊጋ፣ 2 የስፔን የንጉስ ዋንጫ እና 5 የስፔን…
Read More...

አርጀንቲናውያን ተጫዋቾች በፈረንሳይ ተጫዋቾች ላይ የሰነዘሩት የዘረኝት ጥቃት ከፍተኛ ቁጣ አስነሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች የዘር ሐረጋቸው ከአፍሪካ የሚመዘዝ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ላይ ያነጣጠረ የዘረኝነት ዘፈን ሲዘፍኑ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገፆች ከተሰራጨ በኋላ ከፍተኛ ቁጣ አስነስቷል፡፡ የፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አባላት ‹‹አስፀያፊ፣…

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚጀምርበት ቀን ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መስከረም 10 ቀን 2017 እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ፕሪሚየር ሊጉ የሚጀመርበትን ጊዜ ለተሳታፊ ክለቦች ማሳወቁን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡ የ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሰኔ 29 ቀን 2016 መጠናቀቁ…

ሳውዝጌት ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸው ለቀቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በራሳቸው ፈቃድ ኃላፊነታቸውን ለቀቁ፡፡ ሳውዝ ጌት ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ የእግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከስምንት ዓመታት በኋላም በይፋ ከብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነታቸው መልቀቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ በቡድኑ በነበራቸው ቆይታም በ2024ቱ…

አንሄል ዲ ማሪያ ከአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ራሱን አገለለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀቲናዊው የክንፍ መሥመር ተጫዋች አንሄል ዲ ማሪያ ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት ዋንጫ (ኮፓ አሜሪካ) ድል ማግስት ከብሄራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡ ባለፈው ህዳር ወር ከኮፓ አሜሪካ ውድድር ፍፃሜ በኋላ ከብሄራዊ ቡድኑ እንደሚለያይ አስታውቆ የነበረው የ36 ዓመቱ ዲ ማሪያ፤ ዛሬ ንጋት ላይ አርጀንቲና ኮሎምቢያን ላውታሮ…

አርጀንቲና የኮፓ አሜሪካን ዋንጫ ለ16ኛ ጊዜ አነሳች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲና በኮፓ አሜሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ኮሎምቢያን በማሸነፍ ለ16ኛ ጊዜ የዋንጫው ባለቤት ሆናለች፡፡ የሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች ጨዋታ በመደበኛ 90 ደቂቃ ያለ ግብ መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርቷል፡፡ በዚህም ላውታሮ ማርቲኔዝ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ አርጀንቲና 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡…

የባለስልጣናት ቡድን የባለሀብቶችን ቡድን 2 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመቻል ስፖርት ቡድን 80ኛ ዓመት ምስረታ አከባበር በተካሄደ የእግር ኳስ ጨዋታ የባለስልጣናት ቡድን የባለሀብቶችን ቡድን 2 ለ 1 አሸንፏል። “መቻል ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ ያለውን የመቻል ስፖርት ክለብ 80ኛ ዓመት ምስረታ ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና…