Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

እሁድ ሊካሄድ የነበረው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊታችን እሁድ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል ሊደረግ የነበረው የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ተራዘመ፡፡ ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ሊከናወን ታስቦ የነበረ ቢሆንም ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
Read More...

‘አሰልጣኟ አይደለህም፣ አናውቅህም’ ተብየ ኦሊምፒኩን እንዳልከታተል ተደርጌያለሁ – የአትሌት ጽጌ ዱጉማ አሰልጣኝ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘አሰልጣኟ አይደለህም፣ አናውቅህም’ ተብየ ኦሊምፒኩን እንዳልከታተል ተደርጌያለሁ ሲል የአትሌት ጽጌ ዱጉማ አሰልጣኝ ዓለሙ ዋቅጅራ ተናገረ፡፡ አሰልኙ የፓሪስ ኦሊምፒክ መለያ ባጅ መከልከሉን ተክትሎ በኢትይጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አመራሮች ላይ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረገው አሰልጣኝ…

በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ሩጫ አትሌት ሐጎስ ገብረ ሕይወት፣ ቢንያም መሐሪ እና አዲሱ ይሁኔ ለፍጻሜ አልፈዋል፡፡ የ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ማጣሪያ ውድድር 6 ሰዓት ከ10 ላይ ተካሂዷል፡፡ በዚህም አትሌት ሐጎስ በምድብ አንድ 2ኛ እንዲሁም በምድብ ሁለት ቢንያም መሐሪና አዲሱ ይሁኔ በቅደም ተከተል…

ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት የ3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል ፍጻሜ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ የዛሬ መርሐ-ግብሮች ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍጻሜ እና የማጣሪያ ውድድሮች ይካሄዳሉ፡፡ በዚሁ መሠረት ምሽት 4 ሠዓት ከ43 ላይ በሚካሄደው 3 ሺህ ሜትር የወንዶች የፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ለሜቻ ግርማ፣ ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት ዋለ ይሳተፋሉ፡፡ እንዲሁም ቀን 6 ሠዓት ከ10 ላይ በሚካሄደው…

በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፉ። ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት ከ5 ላይ በተካሄደው 1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የማጣሪያ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይና ድርቤ ወልተጂ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል። በዚህም ጉዳፍ…

ኢትዮጵያ የምትካፈልበት 3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ፍጻሜ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ የዛሬ መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ምሽት 4 ሠዓት ከ10 ላይ ትሳተፋለች፡፡ በዚሁ መሠረት በፍጻሜ ውድድሩ አትሌት ሎሚ ሙለታ እና ሲምቦ ዓለማየሁ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡ ከትናንት በስቲያ በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር አትሌት ሎሚ 9 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ ከ73 ማይክሮ…