ስፓርት
በቻምፒየንስ ሊጉ ሪያል ማድሪድ ሲሸነፍ ባየርሙኒክ እና ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎች በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ተደርገዋል።
ከምድብ አንድ እስከ አራት በሚገኙ ቡድኖች መካከል በተደረጉ ጨዋታዎች ያልተጠበቁ ውጤቶችም ተመዝግበዋል።
በምድብ አንድ ሎኮሞቲቭ ሞስኮን ያስተናገደው ሳልዝበርግ ጨዋታውን ሁለት አቻ ሲያጠናቅቅ ዞቦዝላይ እና ጁኑዞቪች ለሳልዝበርግ እንዲሁም ሎፔዝ እና ሊሳኮቪች ለሎኮሞቲቭ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
አሊያንዝ አሬና ላይ በተካሄደው የምድቡ ሌላኛ ጨዋታ ባየር ሙኒክ አትሌቲኮ ማድሪድን 4 ለ 0 በሆነ…
Read More...
በቻምፒየንስ ሊጉ ጁቬንቱስ፣ ማንቼስተር እና ባርሴሎና ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 11 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት በተለያዩ ከተሞች ተካሄደዋል፡፡
ከምድብ አምስት እስከ ስምንት በሚገኙ ቡድኖች መካከል በተደረገው ጨዋታ ታላላቆቹ ቡድኖች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በምድብ አምስት የተደረጉ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ፥ ቼልሲ ከሲቪያ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል፡፡…
አትሌት ሃጎስ በጣልያን በተካሄደ የ10 ሺህ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጣልያን በተካሄደ የ10 ሺህ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት ሃጎስ ገብረህይወት የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸናፊ ሆኗል፡፡
አትሌት ሃጎስ ርቀቱን 29 ደቂቃ ከ49 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸንፏል፡፡
የቀድሞው የቦታው ክብረ ወሰን 30 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ እንደነበር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ…
ዋልያዎቹ በቀጣይ ሳምንት ከዛምቢያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በቀጣይ ሳምንት ከዛምቢያ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
የወዳጅነት ጨዋታው ጥቅምት 12ና 15 ቀን 2013 በአዲስ አበባ ስታድየም እንደሚካሄድ ነው የተገለፀው።
ብሄራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ…
የኮማንደር አሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ “አዳኙ አሰልጣኝ” መጽሃፍ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮማንደር አሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ "አዳኙ አሰልጣኝ" መጽሃፍ በዛሬው እለት ተመርቋል።
በመጽሃፉ ምረቃ ላይም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎች ተገኝተዋል።…