Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የኢትዮጵያና የኒጀር የመልስ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲካሄድ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ እና የኒጀር የመልስ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም በዝግ እንዲካሄድ መወሰኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ። የመልስ ጨዋታው በባሕር ዳር ስታዲየም ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት እንደነበር ይታወሳል። ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም እንዲካሄድ ለአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ካፍ) ጥያቄ አቅርባ ነበር። ካፍም ጥያቄውን ተቀብሎ ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታድየም በዝግ እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላልፏል። ኒጀር ላይ በተደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ ኒጀር 1 ለ…
Read More...

የሲዳማ ክልል የስፖርት ምክር ቤት የምሥረታ ጉባዔ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የስፖርት ምክር ቤት የምሥረታ ጉባዔ ተካሄደ። በጉባዔው ላይ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የተለያዩ ስፖርት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቶችና ጥሪ የተደረገላቸው…

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ በኒጀር አቻቸው 1 ለ 0 ተሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋልያዎቹ በኒጀር አቻቸው 1 ለ 0 ተሸነፉ:: የኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት ከኒጀር ጋር በኒያሚው ስታድ ጀነራል ሴኒ ስታዲየም አድርገዋል፡፡ በጨዋታው ኒጀሮች ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት በማስቆጠር አሸናፊ ሆነዋል፡፡…

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር  ዶክተር ሂሩት ካሰው በአዲስ አበባ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ብሔራዊ ስታዲየም ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር  ዶክተር ሂሩት ካሰውን  ጨምሮ ከፍተኛ የስፖርት አመራሮች በአዲስ አበባ በመገንባት ላይ የሚገኘውን ብሔራዊ ስታዲየም ጎብኝተዋል ፡፡ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ገርጂ አካባቢ በቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ስራ ተቋራጭነት በኤም ኤች ኢንጅነሪንግ አማካሪነት…

ዋልያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ከሱዳን ጋር አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በወዳጅነት ጨዋታ ከሱዳን አቻው ጋር ተጫውቷል፡፡   ማምሻውን በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡   የመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታው ክፍለ ጊዜ ጌታነህ ከበደ ባስቆጠራት ጎል በዋልያዎቹ መሪነት ቢጠናቀቅም ሱዳኖች በተከታታይ…

ሎዛ አበራ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ፈረመች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሎዛ አበራ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ፈረመች፡፡ የቡድኑ አሰልጣኝ አቶ ብርሀኑ ግዛው ለረጅም ጊዜ ሲከታተሏት እንነበር ገልጸው ተጫዋቿ ቡድናቸውን በመቀለቀሏ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ሎዛ አበራ በበኩሏ ቡድኑን በመቀላቀሏ መደሰቷንና ከሌሎች የቡድን አጋሮቿ ጋር በመሆን ውጤታማ ለመሆን…

የኦሊምፒክ ተሳታፊ  አትሌቶች ከህዳር 1 እስከ 13 ሊዘከሩ ነው

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 26 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሊምፒክ ተሳታፊ ጀግና አትሌቶች ከህዳር 1 እስከ 13  ቀን 2013 ዓ. ም. ድረስ በየተሳተፉባቸው ኦሊምፒኮች ቅደም ተከተል መሠረት ቀን ተሰይሞላቸው እንደሚዘከሩ ተገለጸ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሻምበል አትሌት አበበ ቢቂላን 60ኛ ዓመት የሮም ኦሊምፒክ የማራቶን ድል ምክንያት በማድረግ  ከሜልቦርን እስከ ሪዮ…