ስፓርት
ፋሲል ከነማ ፕሪምየር ሊጉን በድል ሲጀምር ድሬዳዋ ከተማ ከሰበታ ከተማ አቻ ተለያይተዋል
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከፋሲል፤
ድሬዳዋ ከተማ ከሰበታ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ዛሬ ጀምሯል፡፡
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ድሬዳዋ ከሰበታ ከተማ ያለግብ 0 ለ 0 ተለያይተዋል።
9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ሌላኛው ጨዋታ ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።
የፋሲል ከነማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሙጅብ ቃሲም በመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ 44ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።
ነገ እሁድ ከቀኑ 4 ሰዓት ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና ከወልቂጤ…
Read More...
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ሩዋንዳ ኪጋሊ ገባ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ሩዋንዳ ኪጋሊ ገብቷል፡፡
ቡድኑ ቅዳሜ በሚጀመረው እና በሩዋንዳ አስተናጋጅነት በሚካሄደው በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ላይ ለመሳተፍ ነው ኪጋሊ የገባው።
ኢትዮጵያን ጨምሮ 7 ሀገራት የሚሳተፉበት ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከኡጋንዳ፣ ኬንያና…
የዘንድሮ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተሳታፊዎች ቁጥር ወደ 12 ሺህ 500 ዝቅ መደረጉ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ነገ ምዝገባ በሚጀምረው 20ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 12 ሺህ 500 ተሳታፊዎች እንደሚካሄድ ተገለፀ።
የኮቪድ-19 ቅድመ ጥንቃቄዎችን ተቀዳሚ በማድረግ ጥር 2 2013 ዓ.ም የሚካሄደው 20ኛው ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ምዝገባ በነገው እለት እንደሚጀመርም ተገልጿል።
የውድድሩ ምዝገባ ከታህሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም…
የጣልያናዊው እግርኳስ ተጫዋች ፓውሎ ሮሲ ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ጣልያን ዓለም ዋንጫን እንድታነሳ ካስቻሏት ተጫዋቾች መካከል አንዱ የነበረው ፓውሎ ሮሲ ህይወቱ አለፈ፡፡
የ64 ዓመቱ ፓውሎ ሮሲ ጣልያን በ1982 የዓለም ዋንጫን ስታነሳ ብሔራዊ ቡድኑን እየመራ ለድል ካበቁት መካከል አንዱ ነው፡፡
የሮሲን ህልፈት ባለቤቱ ፌዴሪካ ካፔሌቲበኢንስታግራም ገጽዋ ይፋ አድርጋለች፡፡
እስካሁን…
ስፖርት ኮሚሽን በ25 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ የፈረንሳይ ለጋሲዮን ጨፌ ሜዳ ግንባታን አስጀመረ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን በ25 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ የፈረንሳይ ለጋሲዮን ጨፌ ሜዳ ግንባታን አስጀመረ፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 የሚገኘው የፈረንሳይ ለጋሲዮን ጨፌ ሜዳ ግንባታን የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን እና የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ተክሌ በዛሬው ዕለት…
የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር ለጠ/ሚ ዐቢይ የአህጉሩን ከፍተኛ የስፖርት ሽልማት አበረከተ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር /አኖካ/ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአህጉሩን ከፍተኛ የስፖርት ሽልማት /ኦርደር ኦፍ ሜሪት/ አበረከተ።
ሽልማቱ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ለኦሎምፒክ ስፖርት ማደግ ለሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥ ነው።
በርካታ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎች ይህንን ሽልማት ማግኘት ችለዋል።…
አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በቫሌንሺያ የተካሄደውን የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በስፔን ቫሌንሺያ የተካሄደውን የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ገንዘቤ ዲባባ አሸነፈች፡፡
አትሌት ገንዘቤ ግማሽ ማራቶኑን በ1 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ17 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቃለች፡፡
ሁለተኛ የወጣችው ኬንያዊቷ አትሌት ሼይላ ቼፕኪሩ 1 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ39 በሆነ ማይከሮ ሰከንድ ነው የገባችው፡፡
በውድድሩ…