ስፓርት
በባርሴሎና ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2025 የባርሴሎና ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ተስፋዬ ድሪባ በአንደኝት ያጠናቀቀ ሲሆን፤ ርቀቱን ለመጨረስም 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ13 ሰከንድ ፈጅቶበታል፡፡
በዚሁ ውድድር አትሌት ተስፋዬን በመከተል ኬንያውያን አትሌቶች ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡
ኢትዮጵያን የወከሉት አትሌት መኳንንት አየነው እና ካሳሁን ኃይሉ 6ኛ እና 10ኛ ደረጃ ይዘው ውድድሩን ጨርሰዋል፡፡
በተመሳሳይ በሴቶች በተደረገ…
Read More...
የ2017 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን አትሌት ብሬነሽ ደሴ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድርን አትሌት ብሬነሽ ደሴ 1ኛ በመውጣት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡
በውድድሩ አትሌት አብዙ ከበደ 2ኛ እንዲሁም መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተከታትለው ገብተዋል።
የ2017 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ…
የካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ምሽት 1 ሠዓት ከ30 ላይ በዌምብሌይ ስታዲየም በሊቨርፑል እና ኒውካስል ዩናይትድ መካከል ይደረጋል፡፡
ሊቨርፑል በግማሽ ፍፃሜው የሰሜን ለንደኑን ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐርን አሸንፎ ለፍፃሜ መብቃቱ ይወሳል፡፡
እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ሌላኛውን የሰሜን ለንደን ክለብ አርሰናልን አሸንፎ ነው…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር አርሰናል በሜዳው 10 ሠዓት ከ30 ላይ ከቼልሲ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡
በ55 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል፤ ቼልሲን ለማሸነፍ እና ከተከታዮቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት ወደ ሜዳ ይገባል።
በሁሉም ውድድር ባለፉት አራት ጨዋታዎች…
በናንጂንግ በሚካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 14 ኢትዮጵያዊያን ይሳተፋሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና ናንጂንግ በሚካሄደው የዘንድሮው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ 14 አትሌቶች እንደሚሳተፉ ተገለጸ፡፡
የሁለት ጊዜ የሻምፒዮናው ባለክብር መለሰ ንብረት እና ሳሙኤል ተፈራ በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ኢትዮጵያ ይወክላሉ፡፡
በሪሁ አረጋዊ፣ ቢኒያም መሃሪ እና ጌትነት ዋለ በወንዶች 3 ሺህ ሜትር…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር ለቀጣይ ዓመት የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎ ወሳኝነት ያላቸው ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
የቀጣይ ዓመት የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት የሚያልሙት ማንቼስተር ሲቲዎች ምሽት 12 ሰዓት ላይ በኢቲሃድ ብራይተንን የሚያስተናግዱበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በ47 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ…