ስፓርት
በቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶን አትሌት ገርባ ዲባባ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ በተካሄደው የወንዶች ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ገርባ ዲባባ አሸነፈ፡፡
አትሌቱ 21 ኪሎ ሜትሩን 1 ሰዓት ከ26 ሴኮንድ በመግባት ማሸነፍ የቻለው፡፡
ኬኒያውያኖቹ ሙዋንጊ ኮስማስ እና ሪቻርድ ያተር ሪቻርድ 2ኛ እና 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡
በሴቶች የግማሽ ማራቶን ደግሞ ኬኒያዊቷ ሩት ኬፐንጊች 1 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ በመግባት ማሸነፏን ቦነስ ኤይረስ ታይምስ ዘግቧል፡፡
Read More...
በዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስዊዘርላንድ በተካሄደው በሉዛን ዳይመንድ ሊግ በ1 ሺህ 500 ሴቶች ውድድር ፣በ3ሺህ ሜትር ወንዶችና በ3ሺህ ሜትር ወንዶች መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል፡፡
አትሌት ድሪቤ ወልተጂ የ1 ሺህ 500 የሴቶች ውድድርን ቀዳሚ ሆና በመግባት ስታሸንፍ ፍሬወይኒ ሀይሉ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡…
አትሌት ታምራት ቶላ ለችግረኛ ተማሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ስጦታ አበረከተ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ታምራት ቶላ በትውልድ አካባቢው ላሉ ችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ መግዣና ለታዳጊዎች ስፖርት ማጠናከሪያ የሚሆን የ1 ሚሊየን ብር ስጦታ አበርክቷል፡፡
አትሌቱ ዛሬ በትውልድ አካባቢው ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሌልቱ ወረዳ ሚአዋ ከተማ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በዚህ ወቅትም ለችግረኛ ተማሪዎች የትምህርት…
ኢትዮጵያ ቡና በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ አልቻለም
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2024/25 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በኬንያው ኬንያ ፖሊስ በድምር ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።
ሁለቱ ክለቦች ዛሬ አበበ በቂላ ስታዲየም ባደረጉት የመልስ ጨዋታ ኬንያ ፖሊስ 1 ለ 0 አሸንፏል።
ውጤቱን ተከትሎ ኬንያ ፖሊስ በአጠቃላይ ውጤት 1 ለ 0 በማሸነፍ…
አትሌት ታምራት ቶላ በትውልድ አካባቢው አቀበባል ተደረገለት
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ የወንዶች ማራቶን አሸናፊው አትሌት ታምራት ቶላ በዛሬው ዕለት በትውልድ አካባቢው በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሌልቱ ወረዳ ሚአዋ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።
አትሌቱ በከተማው ሲደርስ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የወረዳው አመራሮችና የአትሌቱ ቤተሰቦች የጀግና አቀባበል አድርገውለታል።
አትሌት…
የፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥሉ ቼልሲ ከዎልቨርሃምተን ወንደረርስ እንዲሁም ሊቨርፑል ከብረንትፎርድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ቼልሲ ከዎልቨርሃምተን ወንደረርስ የሚያደርጉት ጨዋታ ቀን 10 ሰዓት ላይ ሲደረግ ሁለቱ ቡድኖች በጨዋታው የመጀመሪያ ጎል እና ነጥብ ይዞ ለመውጣት ወደ ሜዳ ይገባሉ፡፡…
መድፈኞቹ በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ድላቸውን አስመዘገቡ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አስቶንቪላን በሜዳው 2 ለ 0 በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉን ሁለተኛ ድል አስመዝግቧል፡፡
ጎሎቹንም ትሮሳርድ በ67ኛው እንዲሁም ፓርቴ በ77ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
በቅድመ ጨዋታ የማሸነፍ ግምት የተሰጠው አርሰናል ኳስ ተቆጣጥሮ በመጫወት ብልጫ ወስዷል፡፡
በመጀመሪያው ሣምንት…