ስፓርት
ቶተንሃም ሆትስፐርስ ኑኖ ኢስፒሪቶ ሳንቶን አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ለንደኑ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ፖርቹጋላዊውን ኑኖ ኢስፒሪቶ ሳንቶን አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ፡፡
ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ በወልቭስ አራት አመታትን አሳልፈው በውድድሩ አመቱ መጨረሻ ከክለቡ ጋር ተለያይተዋል፡፡
አሰልጣኙ ኤቨርተንን አልያም ክሪስታል ፓላስን ይይዛሉ ተብሎ ቢጠበቅም መዳረሻቸው ሰሜን ለንደን ሆኗል፡፡
ቶተንሃም ባለፈው ሚያዚያ ወር አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆን ካሰናበተ በኋላ የቀድሞ ተጫዋቹ የነበረው ራያን ማሰንን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ክለቡን ይዞ ቆይቷል፡፡…
Read More...
በአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝ እና ዩክሬን ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ ትናንት በተደረጉ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች እንግሊዝ እና ዩክሬን ድል ቀንቷቸዋል፡፡
እንግሊዝ ከጀርመን ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜው ተቀላቅላለች፡፡
የማሸነፊያ ግቦችን ራሂም ስተርሊንግ እና ሃሪ ኬን አስቆጥረዋል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ዩክሬን…
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ::
ድጋፉ ኮሚቴው በጃፓን ቶኪዮ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለሚያደርገው ዝግጅት የሚረዳ መሆኑን የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ድጋፉን ለኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር…
የሴካፋ ውድድር በሁለት ሳምንት ተራዘመ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ውድድር (ሴካፋ) በሁለት ሳምንት መራዘሙን አስታወቀ፡፡
ውድድሩ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሐምሌ 10 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀምር መገለጹን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ፌዴሬሽኑ ውሳኔው የሴካፋ መሆኑን ገልፆ ከውድድሩ መጀመር ሶስት ቀናት በፊት ቡድኖች…
በጣሊያን በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በጣሊያን በተደረገ ጄ ሶል ሙንላይት የግማሽ ማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያውን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል፡፡
በውድድሩ በወንዶች አትሌት ታዬ ግርማ 1 ሰዓት 4 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ዳምጤ ካሹ ታዬ 1 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ከ 13 ሰከንድ በመግባት…
የሴካፋ ውድድር በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሊካሄድ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ 23 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል፡፡
ጨዋታው ከሰኔ 26 እስከ ሀምሌ 11 ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን 11 የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ሀገሮች እና አንድ ተጋባዥ ሀገር በድምሩ 12 አገሮች የሚካፈሉበትን…
የአትሌት አበበ ቢቂላ እና የአትሌት ዋሚ ቢራቱን የኦሳካ ማራቶን ድል ለመዘከር በብሄራዊ ቤተመንግስት የችግኝ ተከላ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አትሌት አበበ ቢቂላ እና አትሌት ዋሚ ቢራቱ በኦሳካ የማራቶን ውድድር ድል የተቀዳጁበትን 60ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በብሄራዊ ቤተመንግስት የችግኝ ተከላ ተካሂዷል።
አትሌት ዋሚ ቢራቱና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በጋራ በመሆን ችግኝ ተክለዋል።
አምባሳደሯ ከአንድ ወር በኋላ በሚካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ…