ስፓርት
ብራዚል በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች እግር ኳስ አሸናፊ ሆነች
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚል በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች እግር ኳስ አሸናፊ ሆነች።
በፍጻሜው ከስፔን ጋር የተገናኘችው ብራዚል ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ብራዚል ተጨማሪ ጎል አስቆጥራ የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች።
ለብራዚል የድል ጎሎቹን ሳንቶስ እና ማልኮም እንዲሁም ኦያርዛባል ደግሞ የስፔንን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦…
Read More...
ጠ/ሚ ዐቢይ በአትሌት ለተሰንበት ግደይ በተመዘገበው ውጤት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር በአትሌት ለተሰንበት ግደይ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘቷ የእንኳን ደስ አለን መልዕክት አስተላለፉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻች መልካም ዕድል ተመኝተዋል፡፡…
የአርባ ምንጭ ከነማ ስፖርት ክለብን ለማጠናከር ያለመ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርባ ምንጭ ከነማ ስፖርት ክለብን ህዝባዊ መሠረት ለማስያዝና የገንዘብ አቅሙን ለማጠናከር በአርባ ምንጭ ከተማ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ ።
ክለቡ በ2014 ዓ.ም በሚደረገው የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተፎካካሪ እንዲሆን ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል።
የአርባ ምንጭ ከነማ ስፖርት ክለብ…
አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳልያ አስገኘች
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ 10 ሺህ ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድር አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳልያ አስገኝታለች።
አትሌት ለተሰንበት ውድድሩን 3ኛ በመሆን አጠናቃለች።
በውድድሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሃሰን 1ኛ ስትሆን ሌላኛዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ቃል ኪዳን ገዛኸኝ 2ኛ በመሆን ውድሯን አጠናቃለች።
በቶኪዮ ኦሊምፒክ 1500 ሜትር ሴቶች ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ፍሬወይኒ ሃይሉ 4ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀቀች
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ 1500 ሜትር ሴቶች ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ፍሬወይኒ ሃይሉ 4ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቃለች፡፡
በውድድሩ ኬንያዊቷ ፌዝ ኪፕዬጎን የኦሎምፒኩን ሪከርድ በመስበር ስታሸንፍ እንግሊዛዊቷ አትሌት ሙዪር ሁለተኛ ወጥታለች፡፡
እንዲሁም ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሲፋን ሀሰን…
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጋና እና ከዚምባቡዌ አቻው ጋር ላለበት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት ለ28 ተጫዋቾች የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጥሪ አድርገዋል፡፡
በዚህም ከኢትዮጵያ ቡና አስራት ቱንጆ ፣አማኑኤል ዮሀንስ፣ ታፈሰ ሰለሞን፣ ዊሊያም ሰለሞንና አቡበከር ነስሩ ሲሆኑ ከወልቂጤ ከነማ ደግሞ…
በቶኪዮ ኦሊምፒክ ዛሬ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሶስት የፍጻሜ ውድድሮች
ይሳተፋሉ አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቶኪዮ ኦሊምፒክ ዛሬ የ5 ሺህ ሜትር የወንዶች፣ 1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶችና የ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ የሴቶች የፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል፡፡
በዚህም ረፋድ 4 ሰአት ከ30 በ20 ኪሎ ሜትር የእርምጃ ውድድር የኋልዬ በለጠው ትወዳደራለች።
9 ሰዓት ላይ ደግሞ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ሚልኬሳ መንገሻ እንዲሁም…