ስፓርት
አትሌት ይታያል ስለሺ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኘ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ይታያል ስለሺ በ17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች በ1 ሺህ 500 ወንዶች አይነ ስውር ጭላንጭል (T-11) ፍጻሜ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።
አትሌቱ ርቀቱን 4 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ከ21 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃ መያዙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
Read More...
ሱዋሬዝ ከመጪው ቅዳሜ ጨዋታ በኋላ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን እንደሚያገል አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዑራጋዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሉዊስ ሱዋሬዝ የፊታችን ቅዳሜ ከሚያደርገው የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ በኋላ ለሀገሩ እንደማይጫወት አስታውቋል፡፡
የ37 ዓመቱ የፊት መስመር ተጫዋች ሀገሩ በመጪው ቅዳሜ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከፓራጓይ ጋር የምታደረገው ጨዋታ የመጨረሻዬ ነው ብሏል፡፡
ለሀገሩ 142 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 69 ጎሎችን…
አትሌት ያየሽ ጌቴ ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች አትሌት ያየሽ ጌቴ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የዓይነ ስውር (T-11) ፍጻሜ ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸነፈች፡፡
አትሌቷ ቀደም ሲል 4 ደቂቃ ከ27 ሰከንድ ከ68 ማይክሮ ሰከንድ በራሷ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን በአራት ሰከንድ በማሻሻል አንደኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ…
ሞሐመድ ሳላህ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሊቨርፑል ጋር ሊለያይ እንደሚችል ፍንጭ ሰጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች ሞሐመድ ሳላህ በ2024/2025 የውድድር ዓመት መጨረሻ ከክለቡ ጋር ሊለያይ እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል፡፡
ትናንት ሊቨርፑል በታሪካዊ ተቀናቃኙ ማንቼስተር ዩናይትድ ላይ ከተጎናጸፈው ድል በኋላ ለስካይ ስፖርት በሰጠው አስተያየት÷ “በዚህ ዓመት መጨረሻ ከሊቨርፑል ጋር ልለያይ…
ሊቨርፑል ማንቼስተር ዩናይትድን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑል ማንቼስተር ዩናይትድን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ምሽት 12ሰዓት በተካሄደው ጨዋታ ሊቨርፑል በሉዊስ ዲያዝ ሁለት ግቦችና በሞ ሳላህ አንድ ግብ ማንቼስተር ዩናይትድን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 9፡30 ኒውካስል ዩናይትድ ከቶተንሃም ባደረጉት ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ 2 ለ 1…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስል ሲያሸንፍ ቸልሲ አቻ ወጥቷል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ኒውካስል ዩናይትድ ሲያሸንፍ ቸልሲ አቻ ወጥቷል፡፡
ቀን 9፡30 ኒውካስል ዩናይትድ ከቶተንሃም ባደረጉት ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
የኒውካስልን ግቦች ሃርቤ ባርነስ እና አሌክሳንደር ኢሳቅ ሲያስቆጥሩ ለቶተንሃም ደግሞ የኒውካስሉ ተጫዋች ዳን በርን በራሱ ግብ…
በፕሪሚየር ሊጉ የላንክሻዬር ደርቢ በኦልድትራፎርድ ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት የላንክሻዬር ደርቢ ጨዋታ ዛሬ 12 ሠዓት ላይ ይደረጋል፡፡
ቀደም ሲል ከተደረጉ ሥድስት የላንክሻዬር ደርቢ ጨዋታዎች ሊቨርፑል አምስቱን እንዲሁም ማንቼስተር ዩናይትድ አንድ ጊዜ አሸንፈዋል፡፡
ግብፃዊው አጥቂ ሞሐመድ ሳላህ በኦልድትራፎርድ መረብ ላይ 14…