Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያ ጂቡቲን 7 ለ 0 ረታች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ውድድር ኢትዮጵያን ከጂቡቲ ባገናኘው መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ድል ቀንቷታል፡፡ በዚሁ መሠረትም ኢትዮጵያ የጂቡቲ አቻዋን 7 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡ ጎሎቹንም÷ ረድዔት አስረሣኸኝ 3፣ ቱሪስት ለማ 2፣ ዕፀገነት ግርማ እና ቤተልሔም በቀለ አንዳንድ ማስቆጠራቸውን ከእግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦…
Read More...

ሉሲዎቹም ከ2022 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ውጪ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ የመጀመርያ ዙር ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ዩጋንዳን 2 ለ0 ማሸነፍ ብትችልም በድምር ውጤት ሉሲዎቹም ከ2022 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ውጪ ሆነዋል። ኢትዮጵያና ዩጋንዳን በድምር ውጤት 2 እኩል መሆናቸውን ተከትሎ በተሰጠ የመለያ ምት ዩጋንዳ 2 ለ1 በማሸነፏ ሉሲዎቹ ከ2022 የአፍሪካ…

ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዮገን የ2014 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ ሆነች

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕየጎን የ2014 ቶታል ኢነርጂ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ እንደምትሆን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታወቀ። አትሌት ፌዝ ኪፕየጎን በ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር በሪዮ እና ቶኪዮ ኦሊምፒክ አሸናፊ መሆኗ ይታወቃል። 2014 ቶታልኢነርጂስ ታላቁ ሩጫ ህዳር 5 ቀን 2014 ዓ.ም…

የቤጂንግ ማራቶን በኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ስርጭት ሳቢያ ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤጂንግ ማራቶን ውድድር የኮቪድ-19 ዴልታ ቫይረስ ስርጭት በሀገሪቱ በፈጠረው ስጋት ምክንያትለሌላ ጊዜ መራዘሙን የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል፡፡   ቻይና ኮቪድ-19 በሀገሪቱ ለሚካሄደው ማራቶን ውድድሩ ስጋት እንዳይሆን እና የሥርጭት ሂደቱን ለማስወገድ በርካት ስራዎች ስትሰራ መቆየቷ ተመላክቷል፡፡…

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ የዓለም ግማሽ ማራቶን ሪከርድን ሰበረች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ለተሰንበት ግደይ ዛሬ በተደረገው የቫሌንሺያ ግማሽ ማራቶን ውድድር የርቀቱን የዓለም ክብረወሰን በመስበር አሸነፈች፡፡ አትሌቷ 1 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ በመግባት ነው አሸናፊ የሆነችው፡፡ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው ውድድሩን ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡…

የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር መር ሃ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት /ሴካፋ/ የ2021 ከ20 ዓመት በታች የሴቶች እግር ኳስ ውድድር በስድስት ሀገራት መካከል እንደሚደረግ የውድድሩ አዘጋጀች አሳውቀዋል፡፡ ከጥቅምት 20 እስከ ጥቅምት 30 / 2014 ዓ.ም በዩጋንዳ በሚካሄደው ውድድር ላይ ስድስት ሀገራት በዙር መልኩ…

ዋልያወቹ ከጋና የሚያደርጉት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በኦርላዶ ስታዲየም ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) እና የጋና የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ ኦርላዶ ስታዲየም እንዲካሄድ ኢትዮጵያ መምረጧን የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ገለፀ:: የባሕር ዳር ስታዲየም በካፍ ከታገደ በኋላ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሀገር ውጭ…