ስፓርት
በጣሊያን በተካሄደ አገር አቋራጭ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አትሌቲክስ ቱር አካል በሆነውና በጣሊያን በተደረገው አገር አቋራጭ የአትሌቲክስ ውድድር አትሌት ዳዊት ስዩምና ይሁኔ አዲሱ በሁለቱም ፆታዎች አንደኛ በመውጣት አሸንፈዋል፡፡
በወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ይሁኔ አዲሱ በ28 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ 1ኛ ደረጃን ይዟል፡፡
በሴቶች 6 ኪሎ ሜትር ዳዊት ስዩም በ18 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ 1ኛ ደረጃን ስትይዝ፣ ፋንታዬ በላይነህ እና መዲና ኢሳ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃ ይዘው ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ…
Read More...
12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ስፖርት ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ስፖርት ፌስቲቫል በጃን ሜዳ መካሄድ ጀምሯል።
በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው፤ የባህል ስፖርቶች ለዘመናዊ ስፖርት መሰረት በመሆናቸው ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።
የባህል ስፖርቶችን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ…
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል፡፡
ከዚህ ቀደም በተፈጠረው የአሰራር ክፍተት ምክንያት ከኢትዮጵያ አግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚነት ታግደው የቆዩት ወይዘሮ ሶፍያ አልማሙን ወደ ስራ አስፈፃሚነት ቦታቸው እንዲመለሱ የውሳኔ ሀሳብ ለጉባኤተኛው ቀርቦ በሙሉ…
የዓለም የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድርን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ ሪከርድ በመስበር አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድርን በሪሁ አረጋዊና እጅጋየሁ ታዬ ሪከርድ በመስበር ጭምር አሸነፉ፡፡
በፈረንጆቹ የ2021 የመጨረሻዋ ቀን በስፔን ባርሴሎና በተደረገ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በሁለቱም ፆታ ኢትዮጵያውያኑ ሪከርድ ሰብረው ማሸነፋቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን…
ዋልያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ሱዳንን አሸነፉ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወዳጅነት ጨዋታ የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን ድል ቀንቶታል።
በካሜሩን ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ማምሻውን ከሱዳን አቻው ጋር የአቋም መለኪያ የወዳጅነት ጨዋታ አድርጓል።
ጨዋታውን ዋልያዎቹ 3 ለ 2 ያሸነፉ ሲሆን፥ የድል ጎሎቹን አማኑኤል ገብረሚካኤል…