Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተካሄደ • በሴቶች አትሌት ያለም ዘርፍ የኋላው፣በወንዶች ደግሞ አትሌት ገመቹ ዲዳ አሸናፊ ሆነዋል።

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 25 ሺህ ሯጮች የሚሳተፉበት 21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በመዲናችን በደማቅ ሁኔታተካሄደ። የ21ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችና ከጎረቤት አገሮች የመጡ አትሌቶች እና የሩጫው ተሳታፊዎች ተገኝተዋዋል። በተካሄደው የአትሌቶች ሩጫ በሴቶች አትሌት ያለም ዘርፍ የኋላው 1ኛ ስትወጣ ግርማዊት ገ/እግዚአብሔር 2ኛ ፣መልክናት ውዱ 3ኛ ውድድሯን አጠናቃለች።…
Read More...

ኢትዮጵያ በታላቁ ሩጫ ላይ ናት! እንኳን ለ21ኛው የታላቁ ሩጫ ዝግጅት አደረሳችሁ- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 21ኛውን የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዝግጅት ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ኢትዮጵያ ድህነትንና ኋላ ቀርነትን፣ ግጭትንና ጦርነትን፣ መለያየትንና መከፋፈልን ከኋላዋ ጥላ፤ ብልጽግናንና ሥልጣኔን፣ ሰላምንና መቻቻልን፣ አንድነትንና መግባባትን ለማስፈን ወደፊት እየሮጠች ነው…

ኅብረተሰቡ ለገቢ ማሰባሰቢያ በተዘጋጀው የእግር ኳስ ጨዋታ እየተዝናና ወገኑን እንዲረዳ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኅብረተሰቡ በኢትዮጵያ ዳያስፖራና የአገር ቤት ቡድን የቀድሞ ታዋቂ ተጫዋቾች መካከል በሚካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ የእግር ኳስ ጨዋታ እየተዝናና ወገኖቹን እንዲረዳ ጥሪ ቀረበ። የኢትዮጵያ ዳያስፖራና የአገር ቤት ቡድን የእግር ኳስ ጨዋታው በመጪው እሁድ ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚካሄድ የዝግጅቱ…

የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በቀጣይ ሳምንት ይጀምራሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ መካሄድ ይጀምራሉ፡፡ የ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የዘጠኝ ሳምንታት ጨዋታዎች በሀዋሳ ከተማ የተካሄዱ ሲሆን ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅትን ተከትሎ ታህሣሥ 15 መቋረጡ ይታወሳል። የሊጉ…

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዛንዚባር ገባ

አዲስ አበባ፣ጥር 13፣2014 (ኤፍ ቢሲ)የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዛንዚባር መግባቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ ከታንዛኒያ አቻው ጋር ለሚያደርገው የ2022 ዓለም ዋንጫ የ4ኛው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ዛሬ ከረፋዱ 4 ሰዓት ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ታንዛኒያ ጉዞውን አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ከ20…

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር ላይ የሚሳተፈውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አበረታቱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር ላይ የሚሳተፈውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አባላትን በአካል በመገኘት አበረታቱ። ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በምታስተናግደው 11ኛው የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር ላይ ብሔራዊ ቡድኗ በሁለቱም ፆታ ለማሳተፍ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።…

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ተሰናበተ፡፡ ዋልያዎቹ ዛሬ ከቡርኪናፋሶ አቻቸው ጋር አንድ እኩል ቢለያዩም በአንድ ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡ ለኢትዮጵያ በፍጹም ቅጣት ምት ብቸኛዋን ጎል በ52ኛው ደቂቃ ላይ ጌታነህ ከበደ አስቆጥሯል፡፡ ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤…