ስፓርት
በአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀቀች።
ምሽቱን ለደረጃ የሚደረግ ፍልሚያ በአዘጋጇ ሀገር ካሜሮንና በቡርኪናፋሶ መካከል ተደርጓል።
ጨዋታው 3 አቻ በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት ያመራ ሲሆን፥ በመለያ ምት ካሜሮን ቡርኪናፋሶን 5 ለ 3 በመርታት ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
በዛረው እለትም በሴኔጋልና በግብፅ መካከል የሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ይጠበቃል።
Read More...
ዛሬ ምሽት ቡርኪናፋሶ እና ካሜሮን ለደረጃ ይጫወታሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው የፍሪካ ዋንጫ መርሃ ግብር መሠረት ቡርኪና ፋሶ እና አዘጋጇ ካሜሮን ለደረጃ ይፋለማሉ።
ጨዋታው ምሽት 4፡00 ላይ በያውንዴ አህመዱ አሂጆ ስቴዲዬም ይካሄዳል።
በሌላ በኩል የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ፍፃሜውን የሚያገኝ ሲሆን፥ በዕለቱም ግብጽ እና ሴኔጋል ለዋንጫ ይፋለማሉ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ…
ግብጽ ወይስ ሴኔጋል – ሁለቱን የሊቨርፑል ኮከቦች በተቃራኒው ያገናኘው የፍጻሜ ጨዋታ
https://www.youtube.com/watch?v=ylQXjMOjUIs
በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን 2 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች፡፡
የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻው 1 ለ 0 ቢሸነፍም ዛሬ በተደረገው ጨዋታ 2 ለ0 በማሸነፍ 2 ለ 1 በሆነ ድምር ዉጤት ወደ መጨረሻው ዙር ማለፍ ችሏል፡፡…
በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛንያን ዛሬ ታስተናግዳለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ2022 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ 4ኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ዛሬ ከቀኑ በ10፡00 ታንዛንያን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ታስተናግዳለች።
ቀደም ሲል አስተያየታቸዉን የሰጡት የቡድኑ አስልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል፥ ከታንዛኒያ መልስ ቡድኑ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆቱን ተናግረዋል፡፡
ይህ ከ20 ዓመት…
ግብፅ ካሜሩንን በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍፃሜ አለፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫው የፍጻሜ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ በመለያ ምት ግብጽ ካሜሩንን 3ለ1 በማሸነፍ ከሴኔጋል በመቀጠል ለፍጻሜ ያለፈች ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡
ግብፅና ካሜሩን ለፍታሜ ጥሎ ማለፍ ባደረጉት ጨዋታ ከ90 ደቂቃው ባሻገር የጭማሪውን 30 ደቂቃ ያለግብ በማጠናቀቃቸው አሸናፊው በመለያ ምት እንዲለይ ተደርጓል፡፡…
በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የዳኝነት ብቃት አድናቆትን ያተረፉት ኢንተርናሽናል ዳኛ በዓምላክ ተሰማ
https://www.youtube.com/watch?v=7iGdY-sH9V4