ስፓርት
ፕሪሚየር ሊጉ ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በኋላ ዛሬ ይመለሳል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በኋላ ዛሬ በሚደረጉ ስምንት ጨዋታዎች ይመለሳል፡፡
በዚሁ መሠረት በአራተኛ ሣምንት መክፈቻ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሳውዝሃምፕተን 8 ሠዓት ከ30 ላይ በሴንት ሜሪ ስታዲየም ይገናኛሉ፡፡
እንዲሁም 11 ሠዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከብሬንትፎርድ፣ ሊቨርፑል ከኖቲንግሃም ፎረስት፣ ብራይተን ከኢፕስዊች ታውን፣ ክሪስታል ፓላስ ከሌስተር ሲቲ፣ ፉልሃም ከዌስትሃም ዩናይትድ፣ አስቶንቪላ ከኤቨርተን ይጫወታሉ፡፡
ምሽት 4 ሠዓት ላይ ደግሞ የአሰልጣኝ…
Read More...
በ5 ሺህ ወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው ገቡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂየም ብራሰልስ በተካሄደ የ2024 ዳያመንድ ሊግ 5 ሺህ ወንዶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ ተከታትለው ገቡ።
በውድድሩ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 12:43.66 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን ቀዳሚ ሆኗል።
አትሌት በሪሁ አረጋዊን በመከተል ሀጎስ ገብረህይወት 12:44.25…
የክሪስቲያኖ ሮናልዶ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ቁጥር 1 ቢሊየን ደረሰ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእግር ኳስ ኮከቡ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮች ቁጥር 1 በሊየን መድረሱ ተገለፀ፡፡
ሮናልዶ 1 ቢሊዮን ተከታይ ያገኘው በሚጠቀማቸው የተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲሆን በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ ተከታይ ያለው የመጀመሪያው ግለሰብ ለመሆን በቅቷል።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ተከታዮቹን ያገኘው…
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በመድፈኞቹ ቤት ለመቆየት የሚያስችላቸውን ውል አራዘሙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በክለቡ ለተጨማሪ ዓመታት የሚያቆያቸውን ውል አራዝመዋል፡፡
በዚሁ መሰረት ስፔናዊው አሰልጣኝ አርቴታ በሰሜን ለንደኑ ክለብ ለተጨማሪ ሦስት ዓመታት ለመቆየት የሚያስችላቸውን ፊርማ ማኖራቸውን አርሰናል አስታውቋል፡፡
ከፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ በኋላ በሰጡት አስተያየትም÷ ኮንትራቱን በማራዘማቸው…
አትሌት ጽጌ ዱጉማ በአሶሳ ለተደረገላት አቀባበል አመሰገነች
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ ኦሊምፒክ በ800 ሜትር የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኘችው አትሌት ጽጌ ዱጉማ በትውልድ አካባቢዋ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ለተደረገላት አባበል አመሠገነች፡፡
ትናንት ወደ አሶሳ የሄደችው አትሌት ጽጌ÷ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ለአደረጉላት አቀባበል እና ለሰጡአት ዕውቅና ምሥጋና…
በፓራሊምፒክ ውድድሮች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ አዲስ አበባ ገባ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል።
ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል…
ዋልያዎቹ በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 2ኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋልያዎቹ በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ይገጥማሉ፡፡
ጨዋታው ምሽት 4 ሠዓት ላይ በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ቤንጃሚን ምካፓ ብሔራዊ ስታዲየም ይደረጋል።
ህመም እና ጉዳት ላይ የነበሩት አብነት ደምሴ እና ወገኔ ገዛኸኝም ዋልያዎቹ ትናንት በአደረጉት የመጨረሻ ልምምድ…