ስፓርት
ለዓለም ዓቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ እጩዎች ተለዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዓለም ዓቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ ሰባት እጩዎች ተለይተው ታወቁ።
የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት እንግሊዛዊው ሎርድ ሰባስቲያን ኮ ከእጩ ተወዳዳሪዎቹ መካከል እንደሚገኙበት ተነግሯል።
በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር በሎስአንጀለስና ሞስኮ ኦሊምፒክ ባለ ድል የነበሩት ሰባስቲያን ኮ በአሁኑ ወቅት የኦሎምፒክ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት የሆኑትን ቶማስ ባችን ለመተካት ከሚወዳደሩ ሰባት እጩዎች ጋር ይፎካከራሉ።
የአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባች በሁለት ዙር…
Read More...
ኢትዮጵያ የካፍ ጠቅላላ ጉባዔን እንድታስተናግድ ተወሰነ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ወሰነ፡፡
ጉባዔው በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እንዲካሄድ ታስቦ የነበረ ቢሆንም÷ ሀገሪቱ ማስተናገድ እንደማትችል ማሳወቋን ተከትሎ ኢትዮጵያ ጉባዔውን ለማካሄድ ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ አጽድቋል፡፡…
አርሰናል ቶተንሃምን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሰናል ቶተንሃምን 1 ለ0 አሸንፏል፡፡
የአርሰናልን ብቸኛ ጎል ያስቆጠረው ገብርኤል ማጋልሀይስ ሲሆን ፥ በ64ኛው ደቂቃ ግብ ላይ አሳርፏል፡፡
በሲድኒ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ ሲድኒ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው በመግባት አሸነፉ።
በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው በሲድኒ ማራቶን አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ 2:21:40 በሆነ ሰዓት በመግባት የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር ውድድሩን አሸንፋለች።
አትሌት ሩቲ አጋ 2:23:09 እንዲሁም አትሌት ጎይተቶም…
ፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ ሲቀጥል ቶተንሃም አርሰናልን ያስተናግዳል
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በሰሜን ለንደን ደርቢ ቶተንሃም ሆትስፐር አርሰናልን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ቀን 10 ሰዓት ላይ ይካሄዳል።
12 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ ዎልቭስ ኒውካስል ዩናይትድን ያስተናግዳል።
ትናንት በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር…
በፕሪሚየር ሊጉ ማንቼስተር ሲቲ ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ሽንፈት አስተናግዷል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ሲያሸንፍ ሊቨርፑል ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢቲሃድ ስቴዲየም ብሬንትፎርድን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የማንቺስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኧርሊግ ሃላንድ ሲያስቆጥር የንቦቹን ብቸኛ ግብ ደግሞ ዮዋኔ ዊሳ አስቆጥሯል፡፡
ኧርሊንግ…
ማንቼስተር ዩናይትድ ሳውዝሃምፕተንን 3 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ሴንት ሜሪ አቅንቶ ሳውዝሃምፕተንን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የማንቼስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ማቲያስ ዴሊት፣ ማረከስ ራሽፎረድ እና አሊሃንድሮ ጋርናቾ አስቆጥረዋል፡፡
8፡30 ላይ በተካሄደው ጨዋታ በሳዝውሃምፕተን በኩል ጃክ ስቴፈንስ በ79…