Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሮማ አሰልጣኝ ዳንዔል ዲ ሮሲን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያኑ ክለብ ሮማ አሰልጣኝ ዳንዔል ዲ ሮሲን ከኃላፊነታቸው ማንሳቱን አስታውቋል፡፡ አሰልጣኙ ከኃላፊነታቸው የተነሱት ሮማን ስኬታማ ማድረግ አልቻሉም በሚል ነው፡፡ ከአደረጓቸው አራት ጨዋታዎች ሦስቱን በአቻ አንዱን በሽንፈት ማጠናቀቃቸውም ዲ ሮሲ እንዲሰናበቱ አድርጓል ተብሏል፡፡ እስከ አሁን ያለውን ውጤት ተከትሎም ሮማ በጣሊያን ሴሪዓ 16ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ዲ ሮሲ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ጆሴ ሞሪኒሆን ተክተው ለሰባት ወራት ሮማን በዋና አሰልጣኝነት…
Read More...

ብራዚላዊው ታዳጊ ኤንድሪክ በሪያል ማድሪድ መለያ በዕድሜ ትንሹ የቻምፒዮንስ ሊግ ግብ አስቆጣሪ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው ታዳጊ ኤንድሪክ ትናንት ምሽት ስቱትጋርት ላይ ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ በሪያል ማድሪድ ታሪክ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ በትንሽ ዕድሜ ግብ አስቆጣሪነት ክብረወሰን ባለቤት ሆኗል፡፡ ኤንድሪክ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የብራዚሉን ክለብ ፓልሜራስን በመልቀቅ ነጭ ለባሾቹን (ማሬንጌዎቹን) መቀላቀሉ ይታወቃል፡፡…

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ዛሬ ሲቀጥል ማንቼስተር ሲቲን ከኢንተርሚላን የሚያገናኘው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ ምሽት 1 ሠዓት ከ45 ላይ የጣሊያኑ ቦሎኛ ከዩክሬኑ ሻካታር ዶኔስክ እንዲሁም የቼክ ሪፐብሊኩ ክለብ ስፓርታ ፕራግ ከኦስትሪያው ሬድቡል ሳልዝበርግ ይገናኛሉ፡፡ በሌላ በኩል የስኮትላንዱ ሴልቲክ ከስሎቫኪያው ስሎቫክ…

ፌዴሬሽኑ ከጎፈሬ ኩባንያ ጋር የዳኞች ትጥቅ አቅርቦት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና ጎፈሬ የትጥቅ አምራች ኩባንያ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የዳኞች ትጥቅ አቅርቦት የአጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል። በፊርማ ሥነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፣ የጎፈሬ መስራችና ባለቤት አቶ ሳሙኤል መኮንን እንዲሁም የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ…

የ2024/25 የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ዛሬ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 36 የአውሮፓ ክለቦችን የሚያሳትፈው አዲሱ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ዛሬ ሲጀመር ኤሲ ሚላን በሜዳው ሳንሲሮ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡ በብዙዎች ያልተወደደው የሻምፒየንስ ሊጉ አዲሱ የውድድር ቅርፅ በአውሮፓ እግር ኳስ የበላይ ጠባቂዎች ይሁንታ ከአገኘ ወዲህ ዛሬ ምሽት መተግበር ይጀምራል፡፡…

አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ስዩም ከበደ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ በታንዛንያ አስተናጋጅነት በሚካሄው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣሪያ ውድድር ላይ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኞች ሹመት ተከናውኗል።…

ለዓለም ዓቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ እጩዎች ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለዓለም ዓቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ ሰባት እጩዎች ተለይተው ታወቁ። የዓለም አትሌቲክስ ፕሬዚዳንት እንግሊዛዊው ሎርድ ሰባስቲያን ኮ ከእጩ ተወዳዳሪዎቹ መካከል እንደሚገኙበት ተነግሯል። በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር በሎስአንጀለስና ሞስኮ ኦሊምፒክ ባለ ድል የነበሩት ሰባስቲያን ኮ በአሁኑ ወቅት…