Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና ናንጂንግ እየተካሄደ በሚገኘው 20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚጠበቁባቸው ሁለት የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ይካሄዳሉ። በዚህ መሰረትም ከቀኑ 8 ሰዓት ከ15 ላይ በሴቶች 3 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ሃይሉ እና አትሌት ብርቄ ሃየሎም ይወዳደራሉ። በተመሳሳይ በወንዶች 3 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ፣ አትሌት ጌትነት ዋለ እና አትሌት ቢኒያም መሐሪ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ33 ላይ ውድድራቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል፡፡…
Read More...

በ1 ሺህ 500 ሜትር ጉዳፍ ጸጋይና ድርቤ ወልተጂ ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ጉዳፍ ጸጋይና ድርቤ ወልተጂ ለፍጻሜ አለፉ፡፡ በቻይና ናንጂንግ እየተካሄደ በሚገኘው ሻምፒዮና፥ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተሳተፉበት የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ተካሂዷል፡፡ በምድብ 1 የተሳተፈችው አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በ4…

ዋልያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከግብፅ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አምስተኛ ጨዋታውን ከግብፅ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያከናውናል። ዋልያዎቹ በምድቡ ካደረጓቸው አራት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ በመያዝ በምድቡ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፤ ተጋጣሚያቸው የግብፅ ብሔራዊ ቡድን በ10 ነጥብ ምድቡን በበላይነት እየመራ ይገኛል።…

15 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች የሚሳተፉበት ሜሪ ጆይ የ5 ኪሜ ሩጫ መጋቢት 28 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍኤምሲ) "አረጋውያንን እመግባለሁ፤ ጤንነቴን እጠብቃለሁ" በሚል መሪ ቃል የበጎ አድራጎት ገቢ ማሰባሰቢያ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር መጋቢት 28/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው። ሁነቱን አስመልክቶ አዘጋጆቹ ሜሪጆይ ኢትዮጵያ እና ብራይት ኤቨንትስ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህም ‹‹ሜሪ ጆይ የ5…

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ጥሩነሺ ዲባባ ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን …

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኩራት የሆኑት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአጭር እና በረጅም ርቀት እንዲሁም ጥሩነሺ ዲባባ የታዳጊዎች እና የአዋቂዎችን ውድድር በአንድ ጊዜ በማሸነፍ ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን ደማቅ ታሪክ ጽፈዋል፡፡ አትሌት ቀነኒሳ የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮናን በአጭር እና በረጅም ርቀት…

በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ቡድን ወደ ቻይና አቀና

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንጆቹ ከመጋቢት 21 እስከ 23 ቀን 2025 በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ወደ ቻይና ናንጂንግ ሌሊት ላይ አቅንቷል። ቡድኑ 12 አትሌቶች፣ ሁለት አሰልጣኞች፣ አንድ ቡድን መሪ፣ አንድ የቴክኒክ ቡድን መሪ፣ አንድ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ እና አንድ ፊዝዮቴራፒስት…

በለንደን ደርቢ አርሰናል ቼልሲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ ቼልሲን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የአርሰናልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሚኬል ሜሪኖ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከአስራ ሁለት ጨዋታዎች በኋላ የማዕዘን ምት ግብ አስቆጥሯል።…