Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ዋልያዎቹ ከጊኒ ጋር በሚያደርጓቸው የምድብ ጨዋታዎች ላይ የቀንና የቦታ ለውጥ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከጊኒ ጋር በሚያደርጋቸው ሦስተኛ እና አራተኛ የምድብ ጨዋታዎች ላይ የቀን እና የቦታ ለውጥ መደረጉ ተገለጸ፡፡ በጨዋታዎቹ ላይ የቦታ እና የቀን ሽግሽግ ማድረግ ያስፈለገው የኢትዮጵያ እና የጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ለካፍ ያቀረቡትን ጥያቄ ተከትሎ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡ በዚሁ መሠረት ሦስተኛው የምድብ ጨዋታ ጊኒ የሜዳዋ ጨዋታን ለማድረግ ያስመዘገበችው ያሞሱክሩ የሚገኘው ስታድ ኮናን ባኒ ወደ…
Read More...

አንቶዋን ግሬዝማን ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች እራሱን አገለለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው ተጫዋች አንቶዋን ግሬዝማን ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ማቆሙን ይፋ አድርጓል፡፡ ተጫዋቹ ከብሔራዊ ቡድኑ መለየቱን በመግለጽ በቀሪ የእግር ኳስ ሕይወቱ ለክለቡ አትሌቲኮ ማድሪድ ትኩረት እንደሚሰጥ አስታውቋል። በፈረንጆቹ ከ2014 ጀምሮ ለሀገሩ ፈረንሳይ መጫወት የጀመረው ግሬዝማን ዓለም ዋንጫን ጨምሮ…

በፕሪሚየር ሊጉ የ3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሦስተኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል። በዚሁ መሠረት 10 ሠዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቐለ 70 እንደርታ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ቅዱስ ጊዮርጊስ በሊጉ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች አንዱን ሲያሸንፍ በአንዱ ተሸንፏል። እንዲሁም መቐለ 70…

ወልቂጤ ከተማ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሰረዘ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከሊጉ መሰረዙን አስታውቋል። ክለቡ ለ2017 የውድድር ዘመን የክለብ ላይሰንሲንግ ምዝገባ እና ሌሎች የተቀመጡ መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ነው ከሊጉ የተሰረዘው፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው ማብራሪያ÷አንድ ክለብ ለ2017 የውድድር ዘመን…

በበርሊን ማራቶን አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በበርሊን 2024 ማራቶን አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ አሸነፈ፡፡ አትሌት ሚልኬሳ ርቀቱን 2 ሠዓት ከ3 ደቂቃ ከ17 ሰከንድ በማጠናቀቅ ውድድሩን ማሸነፍ ችሏል፡፡ እንዲሁም አትሌት ሐይማኖት አለው 2 ሠዓት ከ3 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ በመግባት 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ ማንቼስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ መርሐ-ግርብ ሲቀጥል ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት 10 ሠዓት ላይ ኢፕስዊች ታውን በሜዳው አስቶን ቪላን የሚያስተናግድ ሲሆን÷ አስቶንቪላ የማሸነፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑ በቅድመ-ጨዋታ ግምት እየተገለጸ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል በዛሬው የመጨረሻ ጨዋታ መርሐ-ግብር 12 ሠዓት…

አርሰናል እና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል እና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ በኢሜሬትስ ሌስተር ሲቲን ያስተናገደው አርሰናል 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸነፏል፡፡ ለአርሰናል ሊያንድሮ ትሮሳርድ(ሁለት) እና ጋብሬል ማርቲኔሊ እና ካይ ሀቨርትዝ ሲያስቆጥሩ የሌስተር ሲቲን ሁለት ጎሎች ጄምስ ጀስቲን አስቆጥሯል፡፡…