Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና የመጀመሪያ ቀን ውድድር ኢትዮጵያ 2 የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ እየተካሄደ በሚገኘው የ2024 የአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን ብስክሌተኞች ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው አስገኝተዋል፡፡ ሜዳሊያዎቹ የተገኙት በጽጌ ካህሳይ እና ምዕራፍ ገ/እግዚአብሔር መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
Read More...

ኤሊዩድ ኪፕቾጌ በድጋሚ የዩኔስኮ የስፖርት አምባሳደር ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሁለት ጊዜ የኦሊፒክ ሻምፒዮኑ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የስፖርት አምባሳደር ሆኗል፡፡ ኬኒያዊው የማራቶን ባለታሪክ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ ለሁለት ዓመታት ነው የስፖርት አምባሳደር በመሆን የተሰየመው፡፡ የ39 ዓመቱ አትሌት በስፖርት ዘርፍ ላሳየው ዲሲፕሊን እና…

በሞሮኮ የእጅ ኳስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሶስት ክለቦች ትወከላለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሞሮኮ ላዩን ከተማ በሚካሄደው 45ኛው የአፍሪካ ክለቦች የወንዶች እና ሴቶች እጅ ኳስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሶስት ክለቦችን እንደምታሳትፍ ተገለፀ፡፡ በዚህም መሰረት መቻል፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ እጅ ኳስ ክለቦች በመድረኩ ኢትዮጵያን በመወከል ይሳተፋሉ። በወጣው ምድብ መሰረትም መቻል እጅ ኳስ…

የሊቨርፑል የቀድሞ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ወደ እግር ኳስ ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመናዊው የቀድሞ የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በሬድቡል ኩባንያ ስር የሚገኙ የእግር ኳስ ክለቦች ሃላፊ መሆን የሚስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ በሬድ ቡል ኩባንያ ስር በዓለም አቀፍ ደረጃ የጀርመኑ ርቢ ሌብዢግ፣ የኦስትሪያው ሬድ ቡል ሳልዝበርግ፣ የአሜሪካው ኒውዮርክ ሬድ ቡልስ እና በብራዚል ደግሞ ሁለት እግር…

ኮል ፓልመር የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቼልሲው አማካይ ኮል ፓልመር የ2023/24 የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡ የ22 ዓመቱ ፓልመር በሕዝብ በተደረገ ምርጫ የሪያል ማድሪዱን ጁድ ቤሊንግሃም እና የአርሰናሉን ቡካዮ ሳካን በድምፅ በመብለጥ ነው ማሸነፍ የቻለው፡፡ ፓልመር ለሦስቱ አናብስቶች ለመጀመሪያ ጊዜ የተጫወተው…

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል፡፡ በጉባዔው ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ እና የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ንግግር አድርገዋል። የድምፅ ቆጠራ የሚያከናውኑ እና ቃለ ጉባዔ የሚይዙ…

ብራዚል ቤቲንግን ልታግድ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእግር ኳስ ታሪክ ከፍተኛ ስም እና ዝና ያላይ ብራዚል በኦንላይን የሚደረጉ የስፖርት ውርርድን (ቤቲንግ) ልታግድ እንደሆነ አስታወቀች፡፡ ውሳኔው በሀገሪቱ የሚደረጉ የስፖርት ውርርዶች ወደ ሱስነት በመቀየራቸው የተነሳ የተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች መከሰታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል። ከስፖርት ውርርድ ጋር በተያያዘ…