Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሀም ሆትስፐር ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐር ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ በኦልድትራፎርድ ብረንትፎርድን ያስተናገደው የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቡድን ማንቼስተር ዩናይትድ ብረንትፎርድን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ በጨዋታው ብረንትፎርድ በኢታን ፒንኖክ ግብ ቀዳሚ ቢሆንም ከእረፍት መልስ አሊያንድሮ ጋርናቾ እና ራሰመስ ሆይለንድ ባስቆጠሯቸው ግቦች ማንቼስተር ዩናይትድ 2 ለ 1 ማሸነፍ ችሏል፡፡ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐር ዌስትሃም ዩናይትድን 4 ለ 1…
Read More...

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ 7 ጨዋታዎች ያስተናግዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የስምንተኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ 7 ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል፡፡ በዚህም ቶተንሃም ሆትስፐር እና ዌስተሃም ዩናይትድ ከቀኑ 8፡30 የሚጫወቱ ሲሆን ÷ምሽት 1፡30 ላይ ደግሞ በርንማውዝ አርሰናልን የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡ ፉልሃም ከአስቶን ቪላ፣ ኤፕስዊች ታዎን ከኤቨርተን፣ ማንቸስተር…

የካፍ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የካፍ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል፡፡ በዚሁ መሠረት የሴካፋ ሻምፒዮኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ÷ ከደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ፣ ከግብፁ ቱታንካሀሞን እና ከናይጄርያው ኢዲኦ ክዊንስ ጋር በምድብ ቢ ተደልድሏል።

የፕሪሚየር ሊጉ 4ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከነገ ጀምሮ ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 4ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከእረፍት መልስ ከነገ ጀምሮ በድሬዳዋ ስታዲየም በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላል፡፡ በዚሁ መሠረት ነገ 10 ሠዓት ላይ ሀዲያ ሆሳዕና ከሐዋሳ ከተማ እና ምሽት 1 ሠዓት ላይ መቐለ 70 እንደርታ ከመቻል የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ እንዲሁም ከነገ በስቲያ 10 ሠዓት ላይ ስሑል…

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጊኒ ጋር የነበረበትን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ በሽንፈት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡ ብሔራዊ ቡድኑ ከጊኒ አቻው ጋር ያደረጋቸውን ጨዋታቸው በደርሶ መልስ 7 ለ 1 መሸነፉ ይታወቃል፡፡ በነገው ዕለትም ቡድኑ ከጊኒ ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ…

ቶማስ ቱኸል የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመናዊው አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ተሾመዋል፡፡ የቀድሞ የባየርን ሙኒክ እና ቼልሲ አሰልጣኝ የእንግሊዝ ሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን እስከ ፈረንጆቹ 2026 የሚያቆያቸውን ኮንትራት ለመፈረም ከእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ጋር መስማማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ስምምነቱን ተከትሎም…

ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከማንቼስተር ዩናይትድ አምባሳደርነት ሊነሱ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ የቀድሞው ስኬታማ አሰልጣኝና ባለፉት ዓመታት የቡድኑ ዓለም አቀፍ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በዓመቱ መጨረሻ ከኃላፊነታቸው እንደሚሰናበቱ ተሰምቷል፡፡ ሰር አሌክስ ከፈረንጆቹ 2013 ጀምሮ ቀያይ ሰይጣኖቹን በዓለም አቀፍ አምባሳደርነት እንዲሁም ክለቡን በዳይሬክተርነት በማገልገላቸው…