ስፓርት
ሊዮኔል ሜሲ በዓለም አቀፍ ጨዋታዎች የግብ እድሎችን አመቻችቶ የማቀብል ክብረወሰንን ተጋራ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጅንቲናዊው አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም አቀፍ ጨዋታዎች 58 የግብ እድሎችን አመቻችቶ የማቀብል ክብረወሰንን ከቀድሞው አሜሪካዊ አጥቂ ላንደን ዶንቫን ጋር ተጋርቷል፡፡
ሜሲ ትላንት ምሽት በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አርጀንቲና ፔሩን 1 ለ 0 ባሸነፈችበት ምሽት ለቡድን አጋሩ ላውታሮ ማርቲኔዝ ግብ የሆነችዋን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል፡፡
ይህን ተከትሎም በዓለም አቀፍ ጨዋታዎች 58 የግብ እድሎችን በመፍጠርና አመቻችቶ የማቀብል ክብረወሰንን ከላንደን ዶንቫን ጋር መጋራት ችሏል፡፡
የቀድሞው…
Read More...
ፔፕ ጓርዲዮላ በማቺስተር ሲቲ ለመቆየት ተስማማ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ሲቲ አሰልጣኝ ጆሴፍ ፔፕ ጓርዲዮላ በክለቡ ለቀጣይ አንድ ዓመት የሚያቆየውን የውል ማራዘሚያ ለመፈረም መስማማቱ ተነገረ፡፡
የ53 ዓመቱ ስፔናዊ አሰልጣኝ በፈረንጆቹ 2016 ማንቼስተር ሲቲን ከተቀላቀል ወዲህ ስድስት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ጨምሮ 18 ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡
በእንግሊዝ እግር ኳስ አዲስ…
ዋሊያዎቹ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡
ጨዋታው ምሽት 1 ሠዓት ላይ ኬንሻሳ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም የተደረገ ሲሆን÷ ዋሊያዎቹ በበረከት ደስታና መሐመድኑር ናስር ግቦች 2 ለ 1 አሸንፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን…
ኢትዮጵያ የመጨረሻ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዋን ዛሬ ታደርጋለች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን ትገጥማለች፡፡
ጨዋታው ምሽት 1 ሠዓት ላይ ኬንሻሳ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም ይደረጋል መባሉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻው ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻው 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የታንዛኒን ብሔራዊ ቡድን ሳይመን ሀፒጎድ ምሱቫ እና ፋይሰል ሳሉም አብደላ ባስቆጠሯቸው ጎሎች አሸንፎ ወጥሯል።
በውጤቱ መሰረትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ…
ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ ዛሬ ጨዋታዋን ታደርጋለች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ ታንዛንያን ትገጥማለች።
ጨዋታው ምሽት 1 ሠዓት ላይ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም ይደረጋል።
ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን በጄክ ፖውል ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ58 ዓመቱ አሜሪካዊ የከባድ ሚዛን ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ጄክ ፖውል ጋር ባደረገው ግጥሚያ ተሸንፏል፡፡
ታይሰን ዛሬ ማለዳ ያደረገው ግጥሚያ ራሱን ከፕሮፌሽናል ውድድር ካገለለ ከ19 ዓመታት በኋላ የተከናወነ ነው፡፡
የግጥሚያውን ውጤት ተከትሎም ታይሰን 20 ሚሊየን እና ጄክ ፖውል 40 ሚሊየን ዶላር…