Fana: At a Speed of Life!

ምዕራባውያን ለህዝብ መብትና የተሻለ ህይወት የሚቆሙ ከሆነ ሀገራት ችግሮቻቸውን በራሳቸው አቅም እንዲፈቱ ሊያግዙ ይገባል – በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደር

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምዕራቡ ዓለም አገራት በእርግጥ ለሕዝብ መብትና የተሻለ ሕይወት የሚቆሙ ከሆነ ሀገራት ችግሮቻቸውን በራሳቸው አቅም እንዲፈቱ ማገዝ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ በኢትዮጵያ የኩባ አምባሳደር ሆርጌ ለፌብሬ ኒኮላስ ተናገሩ፡፡
ሀያላን አገሮች በአንድ ሉዓላዊ አገር ላይ የሚጥሉት ማዕቀብ ህዝብን ለከፋ ችግር እና ስቃይ የሚዳርግ የጭካኔ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በማንኛውም ሉዓላዊ አገር ላይ ማዕቀብ በመጣል ብዙሃኑን ህዝብ ተጎጂ ከማድረግ አስቀድሞ ችግሮችን ለመፍታት የዲፕሎማሲ ጥረት ትልቅ ሥፍራ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡
አምባሳደር ሆርጌ ለፌብሬ ኒኮላስ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ሀያላን አገራት በሌሎች ላይ ያልተገባ ማዕቀብ በመጣል ህዝብን ለከፋ ችግርና ስቃይ እየዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
ማዕቀብ አድራጊዎቹ “የህዝቡን ህይወት ለማሻሻል ነው” የሚል መልእክት እያስተላለፉ ቢሆንም÷ ብዙሃኑን ህዝብ በተጨባጭ ለስቃይና ችግር እየዳረጉት መሆኑን ገልጸዋል።
“ብዙሃኑን ህዝብ በረሃብ እየቀጡ የፖለቲካ ግብ ማሳካት አይቻልም” ያሉት አምባሳደሩ÷ በአንድ ሉዓላዊት አገር ላይ የሚጣል ማዕቀብ ህዝብን ለከፋ ችግር እና ስቃይ የሚዳርግ የጭካኔ ተግባር መሆኑንም ጠቅሰዋል።
አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት የራሳቸውን የዴሞክራሲ አካሄድ ለሁሉም ሀገራት ለክተው መስጠት ስለሚፈልጉ ሌሎች አገራት በራሳቸው መንገድ ዴሞክራሲን እንዲለማመዱ የማይፈቅድ አካሄድን ይከተላሉ ነው ያሉት፡፡
አገራት የራሳቸው ችግር ሊኖራቸው ይችላል፤ ሁሉም አገሮች ግን ችግሮቻቸውን በራሳቸው መፍታት እንደሚችሉ ጽኑ እምነት እንዳላቸውም ነው አምባሳደሩ የተናገሩት፡፡
የኃያላን አገራት ትኩረት ከዲፕሎማሲ ይልቅ በማዕቀብ ላይ ያተኮረ በመሆኑ ለህዝብ የመፍትሄ አማራጭ ከመሆን ይልቅ የችግርና ስቃይ መንስኤ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.