Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመረጃ ቋት ማዕከል እየገነባ መሆኑን ገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመረጃ ቋት ማዕከል እየገነባ መሆኑን አስታውቋል።

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተካሄደው የህልውና ዘመቻ ምክንያት በተለይ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎችና ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራን እንዲሁም ከዚህ በፊት ከዩኒቨርሲቲዎቹ የተመረቁ ተማሪዎች አሁን ላይ የትምህርትና የስራ ማስረጃዎቻቸውን ማግኘት ባለመቻላቸው መቸገራቸውን ይናገራሉ።

ፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የቀድሞ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህራን÷ አሁን ላይ ትምህርታቸውን ለማሻሻል እንዲሁም የደረጃ እድገት ለማሰራት የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃዎቻቸውን ማግኘት ባለመቻላቸው መቸገራቸውን ነው የሚገልጹት ፡፡

ችግሩ የተፈጠረው ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችና የመምህራንን መረጃ ማግኘት የሚችልበት ስርዓት ባለመዘርጋቱ ነው ያሉት መምህራኑ ÷ የሚመለከተው አካል ጉዳዩን በትኩረት ሊያጤነው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኤባ ሚጀና በበኩላቸው ÷ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሁን ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መረጃዎች ማግኘት የሚያስችለውን የመረጃ ቋት መገንባት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መረጃ ቋቱ ያላቸውን የተማሪዎች፣ የመምህራን እና የምርምር ውጤቶች የያዙ መረጃዎቻቸውን ማስገባት ጀምረዋል ነው ያሉት።

በተጨማሪም ከዚህ በፊት በትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ ለነበሩና አሁን በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙ ተመራቂ ተማሪዎች የመመረቂያ ሰርተፍኬት እያዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

በዘመን በየነ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.