Fana: At a Speed of Life!

ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አገር በቀል የምርምር ውጤቶች ትልቅ ትኩረት መስጠት ይገባል – ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ አገር በቀል ለሆኑ የምርምር ውጤቶች ከፍተኛ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ አስታወቁ፡፡

“የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂና የፈጠራ ስራዎችን በማሸጋገርና በማስፋፋት ኢንዱስትሪውን እናዘምናለን” በሚል መሪ ቃል በሚኒስቴሩና በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ለሁለት ቀናት በአዳማ የሚካሄደውን ዓውደ ጥናት ሲከፍቱ እንደተናገሩት ፥ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው የሚካሄዱ የምርምር የፈጠራና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ለውጤት ማብቃት ለነገ የሚባል ሥራ አይደለም፡፡

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ በበኩላቸው ፥ አገር በቀል የሆኑ የምርምርና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማበረታታትና ማስረፅ የኢንደስትሪውን ተወዳዳሪነት ከማሳደግ ባሻገር በማህበረ ኢኮኖሚው ውስጥ የሚጫወተውን ሚና ከፍ በማድረግ በኩልም የሚኖረው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዓውደ ጥናቱ ላይ ከ14 በላይ የፈጠራ የምርምርና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለኤግዚቢሽን የቀረቡ ሲሆን፥ የከተማና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትና የዘርፉ ማህበራት አመራሮች እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች መገኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.