Fana: At a Speed of Life!

ለአፍሪካ የተለያዩ ተቋማትና ኤምባሲዎች የተሰጡ ቦታዎች በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ አስፈላጊውን ድጋፍ ይደረጋል- አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአፍሪካ የተለያዩ ተቋማትና ኤምባሲዎች የተሰጡ ቦታዎች በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
 
የውጭ ጉዳይ ሜኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ መካሄድ የጀመረውን 40ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
 
በመግለጫቸውም ጉባኤው በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየመከረ እንደሆነ አምባሳደሩ አመላክተዋል፡፡
 
በአህጉራዊ ሰላምና መረጋጋት፣ በኮቪድ-19 መከላከልና መቆጣጠር፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በአጀንዳ 2063 አፈጻጸም እንዲሁም በበጀት አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት መካሄዱን ገልጸዋል።
 
ለአፍሪካ የተለያዩ ተቋማትና ኤምባሲዎች የተሰጡ ቦታዎች በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ መተላለፉን ያስታወሱት አምባሳደር ዲና÷ በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ የኢትዮጵያ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
 
በጉባኤው ላይ ኢትዮጵያ ባቀረበችው ጽሁፍ ለሰብዓዊ መብት መከበር ያላትን ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጧን ኢዜአ ዘግቧል።
 
በሰሜን ኢትዮጵያ ተከስቶ በነበረው ጦርነትም ተፈጸመ የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከተመድ የሰብዓዊ መብት ተቋም ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በጥምረት ማጣራቱን አስታውሰዋል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.