ግድቡ በመጭው ክረምት የቅድመ ምርት እንደሚጀምር ተገለጸ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመጭው ክረምት የቅድመ ምርት እንደሚጀምር ተገለጸ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማትና ሲቪክ ማህበራት ጋር በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ተወያይቷል፡፡
በውይይቱ ላይ ግድቡ በክረምቱ የቅድመ ምርት እንደሚጀመር የተገለጸ ሲሆን፥ ለዚህ የሚያግዝ የ650 ኪሎ ሜትር መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል ነው የተባለው፡፡
ከዚህ ባለፈም ግድቡ በመጭው ክረምት 13 ነጥብ 5 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ የሚይዝ ሲሆን፥ ይህም ግድቡ በአጠቃላይ የሚይዘውን የውሃ መጠን 18 ነጥብ 4 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያደርሰዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በውይይቱ ላይ የሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ወቅቱን ጠብቆ እንደሚከናወንም ነው የተገለጸው፡፡
አሁን ላይ የግድቡ ግንባታ 80 በመቶ የደረሰ ሲሆን፥ የሲቪል ስራው 91 ነጥብ 8 በመቶ፣ የኤሌክትሮ መካኒካል 54 ነጥብ 5 በመቶ እንዲሁም ሃይድሮሊክ ስትራክቸር 55 ነጥብ 2 በመቶ መድረሱ ተገልጿል፡፡
የግድቡ መጠናቀቅም የሃገሪቱን የኢነርጅ ሃይል በሰአት ከ73 ኪሎ ዋት ወደ 220 ኪሎ ዋት ያሸጋግረዋል ተብሏል፡፡
የግድቡን የሙሌት ሂደት ለማደቀናቀፍ የሚደረጉ ጥረቶችን፣ የኦፕሬሽን እና የውሃ አለቃቀቅ ሂደቶችን ኢትዮጵያ ፈጽሞ እንደማትቀበልም ነው የተነሳው፡፡
የሃይማኖትና የሲቪክ ማህበራቱም ለግድቡ እውን መሆን እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
በብስራት መለሰ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!