Fana: At a Speed of Life!

የአሸባሪው ቡድን ሀገር የማፍረስ ፍላጎት በኢትዮጵያ ልጆች የተባበረ ክንድ ድባቅ ይመታል-የአፋር ክልል ሴቶች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ሀገር የማፍረስ ፍላጎት በኢትዮጵያ ልጆች የተባበረ ክንድ ድባቅ ይመታል ሲሉ የአፋር ክልል ሴቶች ገለጹ።

ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተወጣጡ ሴቶች በሰመራ ከተማ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ የአሸባሪውን ህወሓት ቡድንን ሀገር የማፍረስ ሴራ ከመከላከያና ልዩ ሀይሎች ጎን በመሰለፍ ለማክሸፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን በላቀ የሀገር ፍቅር ስሜት ገልጸዋል።

በአሸባሪው ፊት-አውራሪነት በንጹሃን ህጻናት፣ ሴቶችና አረጋውያን ላይ የሚፈጸመውን ግድያ የአለም ህዝብ ሊያወግዘው ይገባል ብለዋል።
“ትውልዱ የአባቶቻችንን አደራ አያጥፍም፣ ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ፣ የጁንታው ሀገር የማፍረስ ፍላጎት በልጆቿ የተባበረ ክንድ ድባቅ ይመታል” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የክልሉ ሴቶች በአሸባሪው ህወሓት ላይ መንግስት በጀመረው የህልውና ዘመቻ እስ ከህይወት መስዋዕትነት በመከፈል ታሪካዊ አደራቸውን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሰልፈኞቹ በሰመራ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች በመዘዋወር አሸባሪው የህወሃት ቡድን የጥፋት ድርጊት የሚያወግዙና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.