የተለያዩ ተቋማት ለመከላከያ ሠራዊት ልዩ ልዩ ድጋፎችን አደረጉ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት የሀገር አንድነት ለማስጠበቅ ከአሸባሪዎች ጋር እየተዋደቀ ላለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የተለያዩ ድጋፎችን አበርክተዋል።
የቦንጋ ዩንቨርሲቲ 30 በሬዎችና 15 ሚሊየን ብር ድጋፍ ሲያደርግ÷ ህብረት ኢትዮጵያ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር 500 ሺህ ብር እና አማዝ የኤሌክትሮኒክስ ማኑፋክቸሪንግ የግል ኩባንያ ደግሞ 250 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።
በተመሳሳይም ሌሎች ተቋማትና ድርጅቶች የገንዘብና የረሽን ድጋፍ ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡
የቦንጋ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጴጥሮስ ወልደጊዮርጊስ÷ የሀገር ህልውና ለማስከበር ውድ ህይወቱን እየሰዋ ላለው የመከላከያ ሠራዊት የሚያደርጉት ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉጂ ለሠራዊቱ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ያለ ሀገር ግብ የሚደርስ ነገር ባለመኖሩ መላው የሀገሪቱ ህዝብ የሀገር ህልውና ለማስከበር የሚያደርገውን ድጋፍ እስከመጨረሻ አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!