ከጣሊያን ጋር ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የድጋፍና ብድር ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የ1 ቢሊየን 40 ሚሊየን ብር የድጋፍ እና የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አርቱሮ ሉዚ ተፈራርመውታል።
ከስምምነቱ ውስጥ 456 ነጥብ 98 ሚሊየን ብሩ ድጋፍ ሲሆን፥ ቀሪው 575 ነጥብ 72 ሚሊየን ብር ደግሞ ብድር መሆኑ ተገልጿል።
ገንዘቡ ለሸገር ማስዋብ ፕሮግራም፣ ለስራ እድል ፈጠራ፣ በክልሎች ለጤና ትግበራ እና ለሌሎች መሰረተ ልማቶች የሚውል መሆኑ ተመላክቷል።
በአዲሱ ሙሉነህ