Fana: At a Speed of Life!

በ1 ነጥብ 19 ቢሊዮን ብር  የሚገነባው የካሌድ ዲጆ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የግንባታ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በስልጤ ዞን በ1 ነጥብ 19 ቢሊዮን ብር  የሚገነባው የካሌድ ዲጆ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የግንባታ ስምምነት ተፈረመ።

የፕሮጀክቱ የግንባታ ስምምነቱ  ዛሬ  የተፈረመ ሲሆን ÷ስምምነቱን የፈረሙት የመስኖ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር  ሚካኤል መሐሪና የደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤልያስ ቱሮ ናቸው፡፡

በፊርማ ሥነ ሥርኣቱ ላይ የተገኙት የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ÷ተቋራጩ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ በጥራት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ የክልሉ መንግሥትና የዞኑ አስተዳደር ድጋፍ እንዲሁም የተቋራጩ ጥረት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚያም ባለፈ ተቋራጩ  ሥራውን በተያዘለት ጊዜ አጠናቆ እንዲያስረክብ አሳስበዋል፡፡

በመስኖ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሚካኤል መሐሪ በበኩላቸው÷ፕሮጀክቱ በታቀደለት ጊዜና በጀት ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ በተቋራጩ በኩል ጥረት መደረግ እንዳለበት ጠቁመው በኮሚሽኑ በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤልያስ ቲሮ ÷ የተሰጣቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ለግንባታ ከተያዘለት ሁለት ዓመት በፊት ግንባታውን በጥራት አጠናቀን ለማስረከብ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ 1 ሺህ 800 ሄክታር መሬት ማልማት እንደሚቻል ከውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.